Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 23:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን የን​ጉ​ሡን የዳ​ዊ​ትን ሰይ​ፍና ጦር፥ አላ​ባሽ አግ​ሬ​ው​ንም ጋሻ ለመቶ አለ​ቆች ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ካህኑ ዮዳሄ በአምላክ ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮች፣ ትላልቅና ትናንሽ ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ካህኑም ዮዳሄ በጌታ ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተጠብቀው ይኖሩ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለጦር መኰንኖች ሰጣቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ካህኑም ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር አላባሽ አግሬውንም ጋሻ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 23:9
5 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ለሱ​ባን ንጉሥ ለአ​ድ​ር​አ​ዛር አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ጋሻ አግ​ሬ​ዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጣ​ቸው። እነ​ዚ​ህ​ንም የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም በሰ​ሎ​ሞን ልጅ በሮ​ብ​ዓም ዘመን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በወጣ ጊዜ ወሰ​ዳ​ቸው።


ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ከጥ​ፍ​ጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በአ​ን​ዱም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገ​ባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን በእጁ እየ​ያዘ በን​ጉሡ ዙሪያ ከቤተ መቅ​ደሱ ቀኝ እስከ ቤተ መቅ​ደሱ ግራ ድረስ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ቅ​ደሱ አጠ​ገብ እን​ዲ​ቆም አደ​ረገ።


ሌዋ​ው​ያ​ንና ይሁ​ዳም ሁሉ ካህኑ ኢዮ​አዳ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ ሰሞ​ነ​ኞ​ቹን አላ​ሰ​ና​በ​ተም ነበ​ርና እያ​ን​ዳ​ንዱ ከሰ​ን​በት መጀ​መ​ሪያ እስከ ሰን​በት መጨ​ረሻ ሰዎ​ችን ወሰደ።


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos