Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “አሁ​ንም እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በነ​ቢ​ያ​ትህ አፍ የሐ​ሰት መን​ፈ​ስን አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ንተ ላይ ክፉ ተና​ግ​ሮ​ብ​ሃል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ስለዚህ እነሆ፣ እግዚአብሔር በእነዚህ ነቢያትህ አፍ የሐሰት መንፈስ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ጥፋት እንደሚያመጣብህ ተናግሯል”።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ ጌታ በእነዚህ በነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስን አኑሮአል፤ ጌታም በአንተ ላይ ክፉ ተናግሮብሃል።’”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሚክያስም “እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ በእነዚህ በነቢያትህ አንደበት የሐሰት መንፈስ እንዳስቀመጠ ታያለህን? ይህንንም ያደረገው በአንተ ላይ ጥፋትን ስለ ወሰነብህ ነው!” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስን አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በአንተ ላይ ክፉ ተናግሮብሃል።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 18:22
18 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ክፉ እንጂ መል​ካም ትን​ቢት አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝም አላ​ል​ሁ​ህ​ምን?” አለው።


እር​ሱም፥ “ወጥቼ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ የሐ​ሰት መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ታታ​ል​ለ​ዋ​ለህ፤ ይቀ​ና​ሃል፥ ውጣ፤ እን​ዲ​ህም አድ​ርግ” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ሁል​ጊዜ ክፉ እንጂ ከቶ መል​ካም ትን​ቢት አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ ነው” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሡ እን​ዲህ አይ​በል” አለው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​አስ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜ​ስ​ያስ እን​ዲህ ሲል ላከ፥ “የሊ​ባ​ኖስ ኵር​ን​ችት ልጅ​ህን ለልጄ ሚስት አድ​ር​ገህ ስጠው” ብሎ ወደ ሊባ​ኖስ ዝግባ ላከ፤ የሊ​ባ​ኖ​ስም ዱር አው​ሬ​ዎች መጥ​ተው ኵር​ን​ች​ቱን ረገ​ጡት።


ኀይ​ልና ብር​ታት በእ​ርሱ ዘንድ ናቸው፤ ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋ​ልም ለእ​ርሱ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ስት መን​ፈ​ስን ልኮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሰካ​ርም፥ ደም ያዞ​ረ​ውም እን​ዲ​ስት እን​ዲሁ ግብ​ፃ​ው​ያን በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ሳቱ።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


አሁን እን​ግ​ዲህ ለይ​ሁዳ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሚ​ኖሩ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈ​ጥ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ምክ​ር​ንም እመ​ክ​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሁ​ንም ሁላ​ችሁ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና ሥራ​ች​ሁ​ንም አቅኑ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው።”


ነቢ​ዩም ቢታ​ለል፥ ቃል​ንም ቢና​ገር፥ ያን ነቢይ ያታ​ለ​ልሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እጄ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከሕ​ዝ​ቤም ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos