Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አስ​ቀ​ድ​ሞም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ አለ​ቃ​ቸው ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከርሱ ጋራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ቀደም ሲል የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እነርሱን ይቈጣጠር ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 9:20
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ።


ጌታ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዮ​ሴፍ ጋር እን​ዳለ፥ እርሱ የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ እን​ዲ​ያ​ከ​ና​ው​ን​ለት አየ።


የቆ​ሬም ልጅ የአ​ብ​ያ​ሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአ​ባቱ ቤት የነ​በሩ ወን​ድ​ሞቹ ቆሬ​ያ​ው​ያን በማ​ገ​ል​ገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መድ​ረክ ይጠ​ብቁ ነበር። አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰፈር መግ​ቢያ ይጠ​ብቁ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው።


የሌ​ዋ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች አለቃ የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮ​ችን ይጠ​ብቅ ዘንድ የተ​ሾ​መው የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር ነው።


ሙሴም ከየ​ነ​ገዱ አንድ ሺህ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸ​ውና ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ከፊ​ን​ሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋ​ያተ ቅድ​ሳ​ቱና ምል​ክት መስጫ መለ​ከ​ቶ​ችም በእ​ጆ​ቻ​ቸው ነበሩ።


የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር በመ​ብ​ራቱ ዘይት በጣ​ፋ​ጩም ዕጣን ላይ ፥ ሁል​ጊ​ዜም በሚ​ቀ​ር​በው በእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና በቅ​ባቱ ዘይት ላይ ሹም ነው፤ ድን​ኳ​ኑን ሁሉ፥ በእ​ር​ሱም ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ፥ መቅ​ደ​ሱ​ንና ዕቃ​ውን ይጠ​ብ​ቃል።”


የጌ​ድ​ሶን ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ይህ ነው፤ ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው ሥራ​ቸው ሁሉ የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች አገ​ል​ግ​ሎት ይህ ነው፤ እነ​ር​ሱም ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በገ​ለ​ዓድ ምድር ወዳ​ሉት ወደ ሮቤል ልጆ​ችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የካ​ህኑ የአ​ሮ​ንን ልጅ የአ​ል​ዓ​ዛ​ርን ልጅ ፊን​ሐ​ስን ላኩ።


ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንዱ መልሶ፥ “እነሆ፥ መል​ካም አድ​ርጎ በገና ሲመታ የቤተ ልሔ​ሙን የእ​ሴ​ይን ልጅ አይ​ቻ​ለሁ፤ ሰው​የ​ውም ጠቢብ፥ ተዋ​ጊም ነው፤ በነ​ገ​ርም ብልህ፥ መል​ኩም ያማረ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነው” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos