Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 25:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከአ​ሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ናታ​ንያ፥ ኤራ​ኤል፤ እነ​ዚህ የአ​ሳፍ ልጆች የን​ጉሡ ቀራ​ቢ​ዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከአሳፍ ወንዶች ልጆች፤ ዛኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። የአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሡ አመራር ሥር ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ ነበሩ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ ትእዛዝ በታች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ዛኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያና አሳርኤላ ተብለው የሚጠሩት አራቱ የአሳፍ ልጆች ሲሆኑ፥ ንጉሡ ትእዛዝ ባስተላለፈ ቊጥር የእግዚአብሔር መንፈስ ያቀበለውን መዝሙር የሚያሰማው አሳፍ የእነርሱ መሪ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከአሳፍ ልጆች ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ እጅ በታች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 25:2
20 Referencias Cruzadas  

ሌዋ​ው​ያ​ኑም የኢ​ዩ​ኤ​ልን ልጅ ኤማ​ንን፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የበ​ራ​ክ​ያን ልጅ አሳ​ፍን፥ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ከሜ​ራሪ ልጆች የቂ​ሳ​ንን ልጅ ኢታ​ንን፥


አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር።


ዳዊ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም የሚ​ዘ​ምሩ ሰዎ​ችን ለማ​ገ​ል​ገል ለዩ፤ በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውም ሥራ የሚ​ሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


ከኤ​ዶ​ትም የኤ​ዶ​ትም ልጆች፤ ጎዶ​ል​ያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸ​ብያ፥ መታ​ትያ፥ እነ​ዚህ ስድ​ስቱ ከአ​ባ​ታ​ቸው ከኤ​ዶ​ትም ጋር በበ​ገና እየ​ዘ​መሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


እነ​ዚህ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በጸ​ና​ጽ​ልና በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ከአ​ባ​ታ​ቸው ጋራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ወደ ንጉሡ ቀር​በው ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። አሳ​ፍም ኤዶ​ት​ምም ኤማ​ንም ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


ሁሉም ተካ​ክ​ለው፥ ታና​ሹም ታላ​ቁም፥ ለሰ​ሞ​ና​ቸው ዕጣ ተጣ​ጣሉ እነ​ር​ሱም ፍጹ​ማ​ንና የተ​ማሩ ነበሩ።


በቀ​ኙም የሚ​ቆ​መው ወን​ድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳ​ፍም የበ​ራ​ክያ ልጅ፥ የሳ​ምዓ ልጅ፤


አና​ጢ​ዎ​ቹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ይሠሩ ዘንድ መሠ​ረት በጣሉ ጊዜ ካህ​ናቱ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ለብ​ሰው መለ​ከ​ቱን ይዘው፥ የአ​ሳ​ፍም ልጆች ሌዋ​ው​ያን ጸና​ጽል ይዘው እንደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ።


አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘ​ወ​ትር ጣል​ኸን? በማ​ሰ​ማ​ሪ​ያህ በጎች ላይስ ቍጣ​ህን ለምን ተቈ​ጣህ?


አቤቱ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ ስም​ህ​ንም እጠ​ራ​ለሁ፤ ተአ​ም​ራ​ት​ህን ሁሉ እና​ገ​ራ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በይ​ሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእ​ስ​ራ​ኤል ታላቅ ሆነ።


በቃሌ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፥ ቃሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ እር​ሱም አደ​መ​ጠኝ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድ​ምጡ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁ​ንም ወደ አፌ ቃል አዘ​ን​ብሉ።


አቤቱ፥ አሕ​ዛብ ወደ ርስ​ትህ ገቡ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ህ​ንም አረ​ከሱ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደ​ረ​ጉ​አት።


ዮሴ​ፍን እንደ መንጋ የም​ት​መራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድ​ምጥ፤ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ፥ ተገ​ለጥ።


በረ​ዳ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እልል በሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ማ​ል​ክት ማኅ​በር ቆመ፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል።


አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አት​በል፥ ቸልም አት​በል።


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ እጅግ የተ​ወ​ደዱ ናቸው።


ሰውም በአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ውስጥ ወን​ድ​ሙን ይዞ፥ “አንተ ልብስ አለህ፥ አለ​ቃም ሁን​ልን፥ ምግ​ባ​ች​ንም ከእ​ጅህ በታች ትሁን” ቢለው፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos