Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዳዊ​ትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድ​ሶ​ንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራ​ሪም በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው መደ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌርሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዳዊትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድሶንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራሪም በየሰሞናቸው ከፈላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ዳዊት ሌዋውያንን በየጐሣቸው ክፍል መሠረት በሦስት ቦታ መደባቸው፤ እነርሱም ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዳዊትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድሶንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራሪም በየሰሞናቸው ከፈላቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 23:6
18 Referencias Cruzadas  

ከጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ለአ​ዳ​ንና ሰሜኢ ነበሩ።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአ​ሮን ልጆች ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር ነበሩ።


በረ​ኞ​ችም እን​ደ​ዚህ ተመ​ደቡ፤ ከቆ​ሬ​ያ​ው​ያን ከአ​ሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱ​ላም።


የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥


የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት ሜራሪ።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በደ​ስ​ታና በመ​ዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የከ​ፈ​ላ​ቸ​ውን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ሾመ።


ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


አገ​ል​ግ​ሎ​ቱም ተዘ​ጋጀ፤ ካህ​ና​ቱም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ ቆሙ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዳዊት እንደ አዘዘ፥ ልጁም ሰሎ​ሞን እንደ አዘዘ በየ​ሰ​ሞ​ና​ች​ሁና በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ቤቶች ተዘ​ጋጁ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ዳዊት እን​ዲህ አዝዞ ነበ​ርና ካህ​ና​ቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሰሞን ከፈ​ላ​ቸው፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ፥ በካ​ህ​ና​ቱም ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው፤ በረ​ኞ​ቹ​ንም ደግሞ በየ​በሩ ሁሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


የሌዊ ልጆች በየ​ስ​ማ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የተ​ቀ​ቡና እጆ​ቻ​ቸ​ውን የተ​ቀ​ደሱ የአ​ሮን ልጆች ስም ይህ ነው።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos