Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዳዊ​ትም እንደ ገና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አት​ውጣ፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም አት​ከ​ተ​ላ​ቸው፤ ነገር ግን ከኋ​ላ​ቸው ዙረህ ቅረ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት “ዙሪያውን ከብበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ ከኋላቸው በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፦ “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዳዊትም እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “ከኋላ በኩል ዞረህ በሾላ ዛፎች አጠገብ በመሆን አደጋ ጣልባቸው እንጂ በዚህ በኩል ሽቅብ ወጥተህ በመሰለፍ አደጋ አትጣልባቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 14:14
7 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በኋ​ላ​ቸው ዞረህ በሾ​ላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠ​ማ​ቸው እንጂ አት​ውጣ።


ዳዊ​ትም፥ “ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልው​ጣን? በእ​ጄስ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ህን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ውጣ” አለው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደግሞ በኀ​ያ​ላን ሸለቆ ተሰ​በ​ሰቡ።


በሾ​ላ​ውም ዛፍ ራስ ውስጥ የሽ​ው​ሽ​ውታ ድምፅ ስት​ሰማ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ሊመታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይወ​ጣ​ልና በዚ​ያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ” አለው።


እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos