Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 9:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አንበጦቹ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶች ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ደፍተዋል፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አንበጣዎቹም ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ የሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አንበጣዎቹ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፤ በራሳቸውም ላይ ወርቅ የሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፤ ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የአንበጣዎቹም መልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነው፥ በራሳቸውም ላይ ወርቅ እንደሚመስሉ አክሊሎች ነበሩአቸው፥ ፊታቸውም እንደ ሰው ፊት ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 9:7
6 Referencias Cruzadas  

“የመጀመሪያው፣ አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ተመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግሩ እንዲቆም ከምድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ የሰውም ልብ ተሰጠው።


“ስለ ቀንዶቹ ሳስብ ሳለሁ፣ ከመካከላቸው አንድ ሌላ ትንሽ ቀንድ ብቅ ሲል አየሁ፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች ሦስቱ ከፊቱ ተነቃቀሉ፤ ይህም ቀንድ የሰው ዐይኖችን የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበረው።


ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣ መኳንንትሽም በብርድ ቀን በቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ ኵብኵባ ናቸው፤ ፀሓይ ሲወጣ ግን ይበርራሉ፤ ወዴት እንደሚበርሩም አይታወቅም።


እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ ነጭ ፈረስ ቆሞ ነበር፤ ተቀምጦበት የነበረውም ቀስት ይዞ ነበር፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እርሱም እንደ ድል አድራጊ ድል ለመንሣት ወጣ።


ከጢሱም አንበጦች ወጥተው በምድር ላይ ወረዱ፤ እንደ ምድር ጊንጦች ሥልጣን ያለ ሥልጣን ተሰጣቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos