Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 78:65 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፤ የወይን ጠጅ ስካር እንደ በረደለት ጀግናም ብድግ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 ጌታ ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ በወይን ኃይል እንደተበረታታ ጀግና፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 በመጨረሻም እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ተነሣ፤ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ድፍረት እንደሚሰማው ጀግና ሆነ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:65
7 Referencias Cruzadas  

ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።


እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!


ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ።


የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፤ ተነሥ፤ ተነሥ! ኀይልን ልበስ፤ እንዳለፉት ዘመናት፣ በጥንት ትውልዶችም እንደ ሆነው ሁሉ ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ አንተ አይደለህምን?


እግዚአብሔር አምላክሽ በመካከልሽ አለ፤ እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩ ያሳርፍሻል፤ በዝማሬም በአንቺ ላይ ከብሮ ደስ ይሰኛል።”


አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኰብልሎ ወደ አንተ ቢመጣ፣ ለአሳዳሪው አሳልፈህ አትስጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos