7 ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።
7 ይጠጣ ድህነቱንም ይርሳ፥ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ።
7 እነርሱ ድኽነታቸውንና ሥቃያቸውን እንዲረሱ ይጠጡ።
መከራህን ትረሳለህ፤ ዐልፎ እንደ ሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።
የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።
ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣ በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤
“ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
በመንፈስ ተሞሉ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ብክነት ነውና።