Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 13:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይሁዳም ሁሉ የእህሉን፣ የአዲሱን ወይንና የዘይቱን ዐሥራት ወደ ዕቃ ቤቶቹ አስገቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ይሁዳም ሁሉ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህም በኋላ እስራኤላውያን ሁሉ እንደገና ከእህልና ከወይን ጠጅ፥ ከወይራ ዘይትም የሚፈለግባቸውን ከዐሥር አንድ እያወጡ ወደ ቤተ መቅደስ ዕቃ ግምጃ ቤት ማምጣት ጀመሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይሁ​ዳም ሁሉ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይሁዳም ሁሉ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 13:12
9 Referencias Cruzadas  

ካህናቱና ሌዋውያኑም ሙሉ ጊዜያቸውን ለእግዚአብሔር ሕግ አገልግሎት ማዋል ይችሉ ዘንድ፣ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጣቸው አዘዘ።


ትእዛዙ እንደ ወጣ እስራኤላውያን ወዲያውኑ የእህሉንና የአዲሱን ወይን ጠጅ፣ የዘይቱንና የማሩን እንዲሁም የዕርሻውን ፍሬ ሁሉ በኵራት በልግስና ሰጡ፤ ካላቸው ከማንኛውም ነገር ሁሉ ላይ እጅግ ብዙ የሆነ ዐሥራት አውጥተው አመጡ።


በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና።


“ ‘ከዕርሻ ምርትም ሆነ ከዛፍ ፍሬ፣ ማንኛውም ከምድሪቱ የሚገኝ ዐሥራት የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነው።


በቤቴ መብል እንዲኖር፣ እኔንም በዚህ እንድትፈትኑኝ ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጐተራ አስገቡ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “የሰማይን መስኮት የማልከፍትላችሁ፣ የተትረፈረፈ በረከትንም ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የማላፈስስላችሁ ከሆነ ተመልከቱ።


“ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን ትሰርቁኛላችሁ። “እናንተ ግን፣ ‘እንዴት እንሰርቅሃለን?’ ትላላችሁ። “ዐሥራትና መባ ትሰርቁኛላችሁ፤


በየዓመቱ ከዕርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos