Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 17:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እነርሱ ደጋግመው፣ “የእግዚአብሔር ቃል የት አለ? እስኪ አሁን ይፈጸም!” ይሉኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነሆ፦ “የጌታ ቃል ወዴት አለች? አሁን ትምጣ!” ይሉኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሕዝቡ “ኤርምያስ ሆይ! እግዚአብሔር ተናገረ ያልከውን ነግረኸን ነበር፤ ታዲያ ለምን አልተፈጸመም” ብለው ይጠይቁኛል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነሆ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወዴት አለ? አሁን ይምጣ ይሉ​ኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነሆ፦ የእግዚአብሔር ቃል ወዴት አለች? አሁን ትምጣ ይሉኛል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 17:15
7 Referencias Cruzadas  

“በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኵል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ የርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም” ለሚሉ ወዮላቸው!


“የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር፣ ‘ዘመኑ ረዝሟል፤ ራእዩ ሁሉ ከንቱ ሆኗል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው?


የእግዚአብሔርን ቀን ለምትሹ፣ ለእናንተ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትሻላችሁ? ያ ቀን ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።


እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችሁታል። እናንተም፣ “ያታከትነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ? “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነው፤ እርሱም በክፉዎች ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ ወዴት ነው?” በማለታችሁ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos