Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 7:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ይሁዳን እንውረር፤ እንበታትነው፤ ተከፋፍለንም እንግዛው፤ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ‘ይሁዳን እንውረር፤ እንበታትነው ተከፋፍለንም እንግዛው፤ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥበት።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እነርሱም ይሁዳን ለመውጋት፥ ሕዝቡንም አስጨንቀው የእነርሱ ደጋፊ በማድረግ የጣብኤልን ልጅ ሊያነግሡባቸው ወስነዋል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ወደ ይሁዳ እን​ው​ጣና እን​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው፤ ወደ እኛም እን​መ​ል​ሳ​ቸው፤ የጣ​ብ​ኤ​ል​ንም ልጅ እና​ን​ግ​ሥ​ባ​ቸው፤”

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 7:6
12 Referencias Cruzadas  

መላው እስራኤልም ንጉሡ ሊሰማቸው አለመፈለጉን በተረዱ ጊዜ፣ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይስ ልጅ ምን ክፍል አለን? እስራኤል፣ ሆይ፤ ወደ ድንኳንህ ተመለስ፤ ዳዊት ሆይ፤ አንተም የገዛ ቤትህን ጠብቅ።” ስለዚህ እስራኤላውያን ወደ የቤታቸው ተመለሱ።


የንጉሥ ኢዮራም ልጅ፣ የአካዝያስ እኅት ዮሳቤት ግን የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሊገደሉ ከነበሩት ልዑላን መካከል ሰርቃ ወሰደችው። እንዳይገደልም ከጎቶልያ በመደበቅ እርሱንና ሞግዚቱን በአንድ እልፍኝ ሸሸገቻቸው።


“አሁንም እናንተ በዳዊት ዘርዐ ትውልድ እጅ ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ልትቋቋሙ ዐስባችኋል። በርግጥም በሰራዊት ረገድ እጅግ ብዙ ናችሁ፤ አማልክታችሁ ይሆኑ ዘንድ ኢዮርብዓም የሠራቸውንም የወርቅ ጥጆች ይዛችኋል።


ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ ካደረገው ኪዳን የተነሣ፣ የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም መብራት እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶ ነበርና።


ስለዚህ አምላኩ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ አሳልፎ ሰጠው፤ ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ ከሕዝቡም ብዙዎቹን ምርኮኞች አድርገው ወደ ደማስቆ ወሰዷቸው። ደግሞም ለእስራኤል ንጉሥ ዐልፎ ተሰጠ፤ እርሱም ከባድ ጕዳት አደረሰበት።


ክፋት ቢያስቡብህ፣ ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤


በሕዝብህ ላይ በተንኰል አሤሩ፤ በውድ ልጆችህ ላይ በአንድነት ተመካከሩ።


በሰው ልብ ብዙ ሐሳብ አለ፤ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሐሳብ ነው።


የዖዝያን የልጅ ልጅ፣ የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን፣ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ነገር ግን ድል ሊያደርጓት አልቻሉም።


ሶርያ ኤፍሬምና፣ የሮሜልዩ ልጅ ሊያጠፉህ እንዲህ ብለው ተማከሩ፤


ጌታ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘ይህ ምክራቸው አይፈጸምም፤ ከቶም አይደረግም፤


“ይህ ሕዝብ በጸጥታ የሚፈስሰውን የሰሊሆምን ውሆች ትቶ፣ በረአሶንና በሮሜልዩ ልጅ ተደስቷልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos