Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 50:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አስከሬኑን ወደ ከነዓን ምድር ወስደው አብርሃም ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ላይ ከነዕርሻው በገዛው፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ በሚገኘው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፥ እርሷም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልጆ​ቹም ወደ ከነ​ዓን ምድር መለ​ሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆ​ነች ዋሻም ቀበ​ሩት፤ እር​ስ​ዋም በመ​ምሬ ፊት ያለች፥ አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት ዋሻ ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጡያዊ ከኤፍሮን ከእርሽ ጋር የገዛት ዋሻ ናት

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 50:13
14 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ዕርሻውና ውስጡ የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያውያን ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈለት።


ይኸውም በዕርሻው ድንበር ላይ ያለችውን መክፈላ የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ነው፤ በመካከላችሁም የመቃብር ቦታ እንድትሆነኝ በሙሉ ዋጋ እንዲሸጥልኝ ለምኑልኝ።”


ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።


ልጆቹ ይሥሐቅና እስማኤል በመምሬ አጠገብ በምትገኝ በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን ዕርሻ በመክፈላ ዋሻ ቀበሩት፤


ያዕቆብ አባቱ ወዳለበት ወደ መምሬ መጣ፤ አብርሃምና ይሥሐቅ የኖሩባት፣ ቂርያት አርባቅ ወይም ኬብሮን የተባለችው ቦታ ናት።


ይሥሐቅም አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።


ዐብሬህ ወደ ግብጽ እወርዳለሁ፤ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፤ የዮሴፍ የራሱ እጆችም ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል።”


እኔም ከአባቶቼ ጋራ ሳንቀላፋ፣ ከግብጽ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦታ ቅበረኝ።” ዮሴፍም፣ “ዕሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለ።


የያዕቆብ ልጆችም አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤


ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ፣ ከወንድሞቹና ለአባቱ ቀብር ዐብረውት ሄደው ከነበሩት ሁሉ ጋራ ወደ ግብጽ ተመለሰ።


ምናሴም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ “የዖዛ አትክልት” በሚባለው በቤተ መንግሥቱ አትክልት ውስጥ ተቀበረ። ልጁ አሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።


አስከሬናቸውም ወደ ሴኬም ተወስዶ፣ አብርሃም ከዔሞር ልጆች ላይ በጥሬ ብር በገዛው መቃብር ተቀበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos