Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 50:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብጻውያን መራራ ልቅሷቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፦ “ይህ ለግብጽ ሰዎች ታላቅ ልቅሶ ነው አሉ፥” ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት፥ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ አውድማ ለቅሶውን ባዩ ጊዜ “ይህ የግብጻውያን ለቅሶ እንዴት መሪር ነው?” አሉ። በዚህ ምክንያት በዮርዳኖስ ሜዳ ያለው የዚያ ቦታ ስም “አቤል ምጽራይም” ተባለ፤ ትርጒሙም በዕብራይስጥ “የግብጻውያን ለቅሶ” ማለት ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በአ​ጣድ አው​ድማ የሆ​ነ​ውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግ​ብፅ ልቅሶ እን​ዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ስዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፦ ይህ ለግብፅ ሰዎች ታልቅ ልቅሶ ነው አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት እርሱም በዮርዳኖች ማዶ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 50:11
10 Referencias Cruzadas  

ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ መንጎች እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።


አብርሃምም እንዲህ አለው፤ “ምንም ቢሆን ልጄን ወደዚያ እንዳትመልሰው ተጠንቀቅ፤


ያዕቆብም ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በዚህ አገር በሚኖሩት በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ዘንድ እንደ ጥንብ አስቈጠራችሁኝ፤ ጭንቀትም እንዲደርስብኝ አድርጋችኋል። እኛ በቍጥር አነስተኞች ነን፤ ተባብረው ቢነሡብኝና ቢያጠቁኝ እኔና ቤተ ሰቤ መጥፋታችን አይደለምን?”


እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ልቅሶ ተቀመጠ።


የያዕቆብ ልጆችም አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤


እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊት ለፊት፣ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን?


አሁንም ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን ያችን መልካሚቱን ምድር፣ ውብ የሆነችውን ኰረብታማ አገርና ሊባኖስን እንዳይ ፍቀድልኝ።”


ወደ ፈስጋ ተራራ ጫፍ ውጣ፤ ወደ ምዕራብና ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅም ተመልከት። አንተ ዮርዳኖስን ስለማትሻገር፣ ምድሪቱን በዐይንህ ብቻ እያት።


የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፣ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ ዕርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ድንጋይ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos