Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 19:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እነሆ፤ ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ የሆነች ትንሽ ከተማ አለች፤ ወደ እርሷ ልሽሽ፤ በጣም ትንሽ አይደለችም እንዴ? ወደዚያ ብሸሽ እኮ ሕይወቴ ትተርፋለች።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እነሆ ይህች ከተማ ወደ እርሷ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት፥ እርሷም ትንሽ ናት፥ ነፍሴን ለማዳን ወደ እርሷ ሸሽቼ ላምልጥ፥ እርሷ ትንሽ ከተማ አይደለችምን?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ በፍጥነት ሸሽቼ ላመልጥበት የምችል እነሆ አንዲት ትንሽ ከተማ በቅርብ አለች፤ ስለዚህ ሸሽቼ ወደ እርሷ እንድሄድ ፍቀዱልኝ፤ እንደምታዩአት ትንሽ ከተማ ናት፤ ወደ እርስዋ ብሄድ ሕይወቴ ከጥፋት ይድናል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እነሆ፥ ይህች ከተማ ወደ እር​ስዋ ሸሽቶ ለማ​ም​ለጥ ቅርብ ናት፤ እር​ስ​ዋም ትንሽ ናት፤ ነፍ​ሴን ለማ​ዳን ወደ እር​ስዋ ሸሽቼ ራሴን ላድን፤ ሰው​ነ​ቴም ከዳ​ነች ትንሽ አይ​ደ​ለ​ችም፤”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እነሆ ይህች ከተማ ወደ እርስዋ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ናት እርስዋም ትንሽ ናት ነፍሴን ለማዳን ወደ እርስዋ ሸሽቼ ላምልጥ እርስዋ ትንሽ ከተም አይደለችምን?

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 19:20
9 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ለአንቺ ሲሉ እንዲንከባከቡኝ፣ ሕይወቴም እንድትተርፍ፣ ‘እኅቱ ነኝ’ በዪ።”


እነሆ፤ እኔ ባሪያህ አንዴ በፊትህ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርገህልኛል፤ እኔ እንደ ሆንሁ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል።


እርሱም እንዲህ አለው፤ “ይሁን ዕሺ፣ ልመናህን ተቀብያለሁ፤ ያልካትንም ከተማ አላጠፋትም።


ሎጥ በዞዓር መኖርን ስለ ፈራ፣ ከዚያ ተነሥቶ ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋራ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ተራሮች ሄደ፤ መኖሪያውንም ከሁለት ሴት ልጆቹ ጋራ በዋሻ ውስጥ አደረገ።


አመሰግንህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤ ሕግህም ይርዳኝ።


ጆሯችሁን ከፍታችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ ነፍሳችሁም እንድትኖር አድምጡኝ። ለዳዊት በገባሁት በጽኑ ፍቅሬ፣ ከእናንተም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።


ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “አሳልፈው አይሰጡህም፤ ብቻ የምነግርህን የእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ፤ መልካም ይሆንልሃል፤ ሕይወትህም ትተርፋለች።


የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣ ሰዎች አይደነግጡምን? ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos