Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 17:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ስለዚህ ከሰማርያ ማርከው ከወሰዷቸው ካህናት አንዱ ወደ ቤቴል ተመልሶ እግዚአብሔርን እንዴት መፍራት እንደሚገባቸው አስተማራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ስለዚህም ከሰማርያ ተማርኮ የተወሰደ አንድ እስራኤላዊ ካህን ተመልሶ በመሄድ በቤትኤል ተቀመጠ፤ በዚያም ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚገባው አስተማረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ስለዚህም ከሰማርያ ተማርኮ የተወሰደ አንድ እስራኤላዊ ካህን ተመልሶ በመሄድ በቤትኤል ተቀመጠ፤ በዚያም ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚገባው አስተማረው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከሰ​ማ​ር​ያም ካፈ​ለ​ሱ​አ​ቸው ካህ​ናት አን​ዱን ወስ​ደው በቤ​ቴል አኖ​ሩት፤ ያም ካህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከሰማርያም ካፈለሱአቸው ካህናት አንዱ መጥቶ በቤቴል ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርንም እንዴት እንዲፈሩት ያስተምራቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 17:28
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም የአሦር ንጉሥ፣ “ከሰማርያ ማርካችሁ ካመጣችኋቸው ካህናት አንዱን፣ በዚያው እንዲኖር መልሳችሁ ውሰዱትና የአገሩ አምላክ ምን እንደሚፈልግ ሕዝቡን ያስተምር” ሲል አዘዘ።


ያም ሆኖ ግን እያንዳንዱ ወገን በየሰፈረበት ከተማ የራሱን አምላክ ሠራ፤ ያንም ቀድሞ የሰማርያ ሕዝብ በኰረብታው ላይ በሠራው ማምለኪያ እየወሰደ አቆመ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።


እርሱም፣ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አለ።


ተዉአቸው፣ እነርሱ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውር መሪዎች ናቸው፤ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ተያይዘው ጕድጓድ ይገባሉ።”


እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው እንሰግዳለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos