Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 25:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ደም እንዳላፈስስና በገዛ እጄ እንዳልበቀል ዛሬ ስለ ጠበቅሽኝ ስለ በጎ ሐሳብሽ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ደም እንዳላፈስና በገዛ እጄ እንዳልበቀል ዛሬ ስለ ጠበቅሽኝ ስለ በጎ ሐሳብሽ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዛሬው ቀን ደም ከማፍሰስና በቀልንም ከመበቀል የጠበቀኝ መልካም አስተሳሰብሽ የተባረከ ይሁን፤ አንቺም የተባረክሽ ሁኚ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ጠባ​ይሽ የተ​ባ​ረከ ነው። ወደ ደም እን​ዳ​ል​ገባ፥ እጄ​ንም እን​ዳ​ድን ዛሬ የከ​ለ​ከ​ል​ሽኝ አን​ቺም የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ወደ ደም እንዳልሄድ፥ በእጄም በቀል እንዳላደርግ ዛሬ የከለከለኝ አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን፥ አንቺም የተመሰገንሽ ሁኚ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 25:33
12 Referencias Cruzadas  

ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።


“አንድ ሌባ በር ሲሰብር ተይዞ ቢደበደብና ቢሞት፣ ተከላካዩ የደም ባለዕዳ አይሆንም፤


የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።


መቶ ግርፋት ሞኝን ከሚሰማው ይልቅ፣ ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።


የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣ እንደ ወርቅ ጕትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።


ብር በማቅለጫ፣ ወርቅም በከውር እንደሚፈተን፤ ሰውም በአንደበት ምስጋና ይፈተናል።


ሸንጋይ አንደበት ካለው ይልቅ፣ ሰውን የሚገሥጽ ውሎ ዐድሮ ይወደዳል።


ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል።


ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጕዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ማን ነው? ዛሬ ስላደረግህልኝ ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ።


ጌታዬ ሆይ፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤


ጌታዬ የምታዝንበት ምክንያት ወይም የኅሊና ጸጸት አይኖርህም፤ በከንቱ ያፈሰስኸውም ደም ሆነ በገዛ እጅህ የተበቀልኸው የለምና። እግዚአብሔር በጎ ነገር ባደረገልህ ጊዜ እኔን አገልጋይህን ዐስበኝ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos