Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 4:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለትም ቀለብ ይህ ነበር፤ ሠላሳ ኮር ማለፊያ ዱቄት፣ ስድሳ ኮር መናኛ ዱቄት፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ያኽል ምርጥ ዱቄት፥ ዐሥር ሺህ ኪሎ ያኽል መናኛ ዱቄት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ያኽል ምርጥ ዱቄት፥ ዐሥር ሺህ ኪሎ ያኽል መናኛ ዱቄት፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ለቀን ለቀኑ ቀለብ የሚ​ሆን ሠላሳ ቆሮስ መል​ካም ዱቄ​ትና ስድሳ ቆሮስ መናኛ ዱቄት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለሰሎሞንም ለቀን ለቀኑ ቀለብ የሚሆን ሠላሳ ኮር መልካም ዱቄትና ስድሳ ኮር መናኛ ድቄት፥

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 4:22
10 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ የአስተናባሪዎቹን አቋቋምና የደንብ ልብሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።


ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብጽ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።


ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ።


ሰሎሞን ደግሞ ለኪራም ቤተ ሰብ ቀለብ እንዲሆን ሃያ ሺሕ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፣ ሃያ ሺሕ ኮር ንጹሕ የወይራ ዘይት ሰጠው፤ ይህን ባለማቋረጥ በየዓመቱ ለኪራም ይሰጥ ነበር።


እንዲሁም በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ የአስተናባሪዎቹን አቋቋምና የደንብ ልብሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹንና አለባበሳቸውን እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።


በየዕለቱም አንድ በሬ፣ ስድስት ምርጥ በጎችና የተወሰኑ ወፎች፣ በየዐሥሩም ቀን ብዛት ያለው ልዩ ልዩ የወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር። ይህም ሁሉ ሆኖ ለአንድ አገረ ገዥ የተመደበውን ምግብ ከቶ ጠይቄ አላውቅም፤ በሕዝቡ ላይ የተጣለው ሸክም ከባድ ነበርና።


በዕውቀትም ውድና ውብ በሆነ ንብረት፣ ክፍሎቹ ይሞላሉ።


ሀብት በበዛ ቍጥር፣ ተጠቃሚውም ይበዛል፤ በዐይኑ ብቻ ከማየት በቀር ታዲያ፣ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል?


ንጉሡም በየዕለቱ የሚበሉትን ምግብና የሚጠጡትን የወይን ጠጅ ከንጉሡ ማእድ ድርጎ እንዲሰጣቸው አደረገ፤ ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ በንጉሡ አገልግሎት ላይ የሚሰማሩ ናቸው።


አንዳንዶቹን ሻለቆችና ዐምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፣ የቀሩትን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos