Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 2:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እርሷም፣ “የምለምንህ አንዲት ነገር አለችኝና እባክህ ዕሺ በለኝ” አለችው። ንጉሡም፣ “እናቴ ሆይ፤ አላሳፍርሽምና ንገሪኝ” ሲል መለሰላት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እርሷም “እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፤ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽም፤ ጉዳዩ ምንድነው” አላት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እርስዋም “እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፤ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽም፤ ጉዳዩ ምንድን ነው” አላት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እር​ስ​ዋም፥ “አን​ዲት ትንሽ ልመና እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ፊት​ህን አት​መ​ል​ስ​ብኝ” አለች። ንጉ​ሡም፥ “እናቴ ሆይ! ፊቴን አል​መ​ል​ስ​ብ​ሽ​ምና ለምኚ” አላት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እርስዋም “አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ፤ አታሳፍረኝ፤” አለች። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽምና ለምኝ፤” አላት።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 2:20
11 Referencias Cruzadas  

አሁንም አንዲት ነገር እለምንሻለሁ፤ አታሳፍሪኝ” አላት። እርሷም፣ “በል ዕሺ ተናገር” አለችው።


ስለዚህም፣ “ሱነማዪቱን አቢሳን ወንድምህ አዶንያስ ቢያገባትስ?” አለችው።


ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ቅጣቱ ለሰዶም ይቀልላታል።”


“ደግሞም እውነት እላችኋለሁ፤ በምድር ላይ ሁለት ሆናችሁ ስለ ምንም ነገር በመስማማት ብትጠይቁ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላችኋል፤


እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos