1 ነገሥት 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 እርሷም “እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፤ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽም፤ ጉዳዩ ምንድነው” አላት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 እርሷም፣ “የምለምንህ አንዲት ነገር አለችኝና እባክህ ዕሺ በለኝ” አለችው። ንጉሡም፣ “እናቴ ሆይ፤ አላሳፍርሽምና ንገሪኝ” ሲል መለሰላት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 እርስዋም “እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፤ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽም፤ ጉዳዩ ምንድን ነው” አላት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 እርስዋም፥ “አንዲት ትንሽ ልመና እለምንሃለሁ፤ ፊትህን አትመልስብኝ” አለች። ንጉሡም፥ “እናቴ ሆይ! ፊቴን አልመልስብሽምና ለምኚ” አላት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 እርስዋም “አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ፤ አታሳፍረኝ፤” አለች። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽምና ለምኝ፤” አላት። Ver Capítulo |