Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 14:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፤ “ተነሺ፣ የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽ እንዳይታወቅብሽ ሆነሽ፣ ወደ ሴሎ ሂጂ፤ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደምነግሥ የነገረኝ ነቢይ አኪያ እነሆ፤ በዚያ ይገኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢዩ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ።፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፦ “የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢዩ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስቱ ሐኖ​ንን፥ “ተነሺ፥ ራስ​ሽን ለውጪ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እንደ ሆንሽ ማንም አይ​ወቅ፤ ወደ ሴሎም ሂጂ፤ ስለ​ዚ​ህም ሕፃን ከደ​ዌው ይድን እን​ደ​ሆነ ጠይቂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እን​ደ​ም​ነ​ግሥ የነ​ገ​ረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ኢዮርብዓምም ሚስቱን “ተነሺ፤ የኢዮርብዓምም ሚስት እንደ ሆንሽ እንዳትታወቂ ልብስሽን ለውጪና ወደ ሴሎ ሂጂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እንድነግሥ የነገረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 14:2
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ፤ ሰው ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፤ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይት አትቀቢ፤ ለሞተ ሰው ብዙ ጊዜ እንዳዘነች ሴት መስለሽም ታዪ።


በዚያ ጊዜ የኢዮርብዓም ልጅ አብያ ታመመ፤


ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ያላትን አድርጋ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች። በዚህ ጊዜ አኪያ ከማርጀቱ የተነሣ ዐይኖቹ ፈዝዘው ነበር።


ከዚያም ነቢዩ ሄዶ ከመንገድ ዳር በመቆም፣ ንጉሡን ይጠባበቅ ጀመር። የራሱን መጠምጠሚያ ወደ ታች አውርዶ ዐይኖቹን በመሸፈንም፣ ማንነቱ እንዳይታወቅ አደረገ።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “እኔ ልብሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ሌላ ሰው መስሎ ወደ ጦርነቱ ገባ።


የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፣ “እኔ ልብሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው። ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን ለውጦ ሌላ ሰው መስሎ ወደ ጦርነቱ ገቡ።


በኰረብታ ላይ ባሉ ማምለኪያ ስፍራዎችና በተራሮች ዐናት ላይ፣ በየዛፉም ጥላ ሥር መሥዋዕት አቀረበ፤ ዕጣንም ዐጠነ።


የማይገለጥ የተሸፈነ፣ የማይታወቅ የተሰወረ ምንም የለም።


መላው የእስራኤላውያን ማኅበር በሴሎ ተሰበሰቡ፣ የመገናኛውንም ድንኳን እዚያው ተከሉ፤ ምድሪቱም ጸጥ ብላ ተገዛችላቸው።


ስለዚህ ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ መልኩን ለውጦ ከሁለት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄደ። እርሱም፣ “እባክሽ፣ ጠንቍዪልኝ፤ የምነግርሽንም ሰው አስነሺልኝ” አላት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos