Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 119:157 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

157 የሚጠሉኝና የሚያሳድዱኝ ብዙዎች ናቸው፤ እኔ ግን ከሕግህ ፈቀቅ አላልኩም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

157 የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው፤ እኔ ግን ከምስክርህ ዘወር አላልሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

157 ያሳደዱኝና ያስጨነቁኝ ብዙዎች ናቸው፥ ከምስክር ግን ፈቀቅ አላልሁም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 119:157
18 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ ጻድቃን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ አይሉም፤ ንጹሖችም በብርታት ላይ ብርታትን ይጨምራሉ።


እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤ በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም።


ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ እኔ ግን ከትእዛዞችህ ፈቀቅ አላልኩም።


ትዕቢተኞች ዘወትር ያፌዙብኛል፤ እኔ ግን ከትእዛዞችህ አልርቅም።


ብዙ ጠላቶች እንደሚዋጉ በሬዎች ከበውኛል፤ እንደ ባሳን ተዋጊ ኰርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው፤


ክፉ ሰዎች እንደ ውሻ ስብስብ ከበቡኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ።


ጠላቶቼ ምን ያኽል እንደ በዙ እይ፤ ምን ያኽል እንደ ጠሉኝም ተመልከት።


ይህም ሁሉ የደረሰብን አንተን ሳንረሳና ቃል ኪዳንህንም ሳናፈርስ ነው።


ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ያጠቁኛል፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ የሚያሳድዱኝ ብዙዎች ናቸው።


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! የምተማመንብህ መማጸኛዬ አንተ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ ታደገኝ፤ አድነኝም።


በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”


በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋል፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።


ኢየሱስ ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች መጡ፤ እነርሱ ከካህናት አለቆችና ከሕዝብ ሽማግሌዎች የተላኩ ነበሩ።


“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos