Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 25:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 “ምናልባት በመካከልህ የሚኖር አንድ መጻተኛ ባለጸጋ ሲሆን፥ እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ለዚያ መጻተኛ ወይም ከእርሱ ቤተሰብ ለአንዱ ራሱን በባርነት ያስገዛ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 “ ‘በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆንና ከወገናችሁ አንዱ ደኽይቶ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ ወይም ከመጻተኛው ወገን ለአንዱ ራሱን ቢሸጥ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 “በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም በአንተ ዘንድ ለተቀመጠው እንግዳ ወይም ለመጻተኛው የቤተሰብ አባላት ቢሸጥ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 “በአ​ን​ተም ዘንድ የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ወይም እን​ግዳ ሀብ​ታም ቢሆን፥ ወን​ድ​ም​ህም በእ​ርሱ አጠ​ገብ ቢደ​ኸይ፥ ራሱ​ንም ለመ​ጻ​ተ​ኛው፥ ወይም ለእ​ን​ግ​ዳው ወይም ለወ​ገ​ኖቹ ዘር ቢሸጥ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 25:47
7 Referencias Cruzadas  

“ለአሕዛብ ሕዝቦች የተሸጡ አይሁድ ወገኖቻችንን ራሳችን ልንቤዣቸው በማሰብ የሚቻለንን ሁሉ አደረግን፤ እናንተ ደግሞ እነሆ፥ የገዛ ወንድሞቻችሁ የሆኑት አይሁድን ወገኖቻቸው ለሆናችሁት ለእናንተ ባርያዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲሸጡላችሁ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ!” ብዬ ገሠጽኳቸው፤ መሪዎቹም የሚመልሱት ቃል አጥተው ዝም አሉ።


አንድ እስራኤላዊ ድኻ ሆኖ መሬቱን ለመሸጥ ቢገደድ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ሊዋጅለት ይገባዋል።


ሊዋጅለት የሚችል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን ዘግየት ብሎ ሀብት በሚያገኝበት ጊዜ እርሱ ራሱ መዋጀት ይችላል።


እነርሱንም በውርስ ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አገልጋዮቻችሁ ይሆናሉ፤ ከእስራኤላውያን ወገኖቻችሁ መካከል ግን ማንንም በማስጨነቅ አትግዙ።


ከተሸጠም በኋላ እንደገና ተዋጅቶ የመመለስ መብት አለው፤ ስለዚህም ከወንድሞቹ አንዱ ሊዋጀው ይችላል፤


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos