50 ይህም የሚሆነው እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ታች ተመልክቶ እስኪያይ ድረስ ነው።
50 እግዚአብሔር ከላይ፣ ከሰማይ እስኪያይ ድረስ።
50 እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ እስኪመለከት ድረስ።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ከተቀደሰውና ከክቡር መኖሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህ የት አሉ? መልካም ፈቃድህና ርኅራኄህስ የት አለ? እነርሱ ከእኛ ርቀዋል።
ምነው ሰማያትን ከፍተህ ብትወርድ፤ ተራራዎችም አንተን አይተው ምነው በተንቀጠቀጡ፤
ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!
በከተማዬ ውስጥ ባሉት ወጣት ሴቶች ላይ የደረሰውን ክፉ ዕድል በማየቴ የመረረ ሐዘን ደረሰብኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ ውርደታችንንም ተመልከት!