Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 19:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዘግየት ብሎም ሰውየው ወደ ልጅቱ ለመሄድና በማግባባት መልሶ ሊያመጣት ቊርጥ ውሳኔ አደረገ፤ ሲሄድም አገልጋዩንና ሁለት አህዮች ይዞ ነበር፤ እዚያም በደረሰ ጊዜ ልጅቱ ተቀብላ ወደ ቤት አስገባችው፤ የልጅቱም አባት ሰውየውን ባየው ጊዜ በደስታ ተቀበለው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ባሏ ታርቆ ሊመልሳት ወደ እርሷ ሄደ፤ ሲሄድም አሽከሩንና ሁለት አህዮችን ይዞ ነበር፤ ሴቲቱም ወደ አባቷ ቤት አስገባችው፤ አባቷም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀበለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ባሏ ታርቆ ሊመልሳት ወደ እርሷ ሄደ፤ ሲሄድም አሽከሩንና ሁለት አህዮችን ይዞ ነበር፤ ሴቲቱም ወደ አባቷ ቤት አስገባችው፤ አባቷም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀበለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ባል​ዋም ተነሣ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመ​ል​ሳት ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ብላ​ቴና፥ ሁለ​ትም አህ​ዮች ነበሩ። እር​ሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀ​በ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ባልዋም ተነሣ፥ ከእርስዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ ቤቱ ሊመልሳት ፍለጋዋን ተከትሎ ሄደ፥ ከእርሱም ጋር አንድ አሽከር ሁለትም አህዮች ነበሩ። እርስዋም ወደ አባትዋ ቤት አገባችው፥ አባትዋም ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተገናኘው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 19:3
16 Referencias Cruzadas  

በውበቷ ተማርኮ እጅግ ወደዳት፤ እርስዋም እንድትወደው ለማድረግ በፍቅር ቃል አነጋገራት።


ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር የለም፤ እኔ እናንተንና ልጆቻችሁን እመግባችኋለሁ።” በዚህም ዐይነት በመልካም ንግግር በማጽናናት አረጋጋቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ እርስዋም ከእርሱ ተለይታ ሌላ ወንድ ካገባች በኋላ እንደገና መልሶ ሊያገባት ይችላልን? ይህ ቢደረግማ ፈጽሞ ምድርን የሚያረክስ ይሆናል። እስራኤል ሆይ! አንቺ ግን ብዙ ጣዖቶችን ወደሽ ነበር፤ አሁን ደግሞ እንደገና ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽ።


ስለዚህ እንደገና ወደ በረሓ እወስዳታለሁ፤ እዚያም በፍቅር ቃል አባብዬ እማርካታለሁ።


በዚያን ቀን “ባለቤቴ” ብላ እንጂ እንደ በዓል ጣዖት “ጌታዬ” ብላ አትጠራኝም።


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በእርሱ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ ገሥጸው።


አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ቢያመነዝር፤ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤


በለዓም በመሄዱ እግዚአብሔር ተቈጣ፤ በለዓም ሁለቱን አሽከሮቹን በማስከተል በአህያው ላይ ተቀምጦ በሚጓዝበት ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ መንገዱን ዘጋበት፤


እጮኛዋ ዮሴፍ ደግ ሰው ስለ ነበረ፥ ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት አልፈለገም፤ ስለዚህ በስውር ሊተዋት አሰበ።


እርስዋም “ጌታ ሆይ! ማንም የለም” አለች። ኢየሱስም “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ፤ ዳግመኛ ኃጢአት አትሥሪ” አላት።


ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።


ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሶምሶን ሚስቱን ለመጐብኘት አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሄደ፤ አባትዋንም “ሚስቴ ወዳለችበት ክፍል መግባት እፈልጋለሁ” አለው። አባትዋ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም፤


ነገር ግን ልጅቱ ከእርሱ ጋር ተጣልታ በቤተልሔም ወደሚገኘው ወደ አባቷ ቤት ኮብልላ ሄደች፤ በዚያም አራት ወር ቈየች።


ጧትም ጎሕ ሲቀድ ያቺ ሴት መጥታ ባልዋ ባደረበት በሽማግሌው ቤት በር አጠገብ ወደቀች፤ ፀሐይ እስክትወጣም ድረስ በዚያ ነበረች፤


እዚያ እንዲቈይ አደረገው፤ እርሱም ሦስት ቀን በዚያ ቈየ፤ እዚያም እየበሉና እየጠጡ ቈዩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos