Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የእርሱን ስም ብጠራና መልስ ቢሰጠኝም እንኳ አቤቱታዬን ያዳምጣል ብዬ አላምንም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጠርቼው ‘አቤት!’ ቢለኝም፣ ያዳምጠኛል ብዬ አላምንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን ሰማ ብዬ አላምንም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ብጠ​ራው፥ እር​ሱም ቢመ​ል​ስ​ልኝ ኖሮ፥ እንደ ሰማኝ አላ​ም​ንም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን እንደ ሰማ አላምንም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:16
12 Referencias Cruzadas  

“አምላክ ሆይ! አንተ በመጀመሪያ ተናገር፤ እኔም መልስ እሰጣለሁ፤ ወይም እኔ ልናገርና አንተ መልስ ስጠኝ።


ፈገግ ስልላቸው ተዝናኑ፤ ፊቴ ሲበራ የተቋጠረ ፊታቸው ተፍታታ።


ንጹሕ ሆኜ ብገኝ እንኳ፥ ፈራጁ አምላክ እንዲምረኝ እለምነዋለሁ እንጂ መልስ ልሰጠው አልደፍርም።


በዐውሎ ነፋስ ያደቀኛል ያለ ምክንያትም ቊስሌን ያበዛል።


እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ ባመጣን ጊዜ ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለንም ነበር።


መከራ በደረሰብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም አምላኬን ለመንኩት፤ በመቅደሱ ሆኖ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴንም አደመጠ።


ሙሴም ይህን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገረ፤ እነርሱ ግን በወደቀባቸው ጨካኝ ጭቈና ምክንያት መንፈሳቸው ተሰብሮ ስለ ነበረ ሊያዳምጡት አልፈለጉም።


እነርሱም ከደስታና ከአድናቆት ብዛት የተነሣ ገና አላመኑም ነበር። ኢየሱስም “አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁን?” ሲል ጠየቃቸው።


ጌዴዎንም እንዲህ አለው፦ “ጌታዬ ሆይ! ታዲያ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ሁሉ ችግር እንዴት ሊደርስብን ቻለ? አባቶቻችን እንደ ነገሩን እግዚአብሔር ያደርገው የነበረ ድንቅ ሥራ ሁሉ ዛሬ የት አለ? ከግብጽ እንዴት እንዳወጣቸውም ነግረውን ነበር፤ ዛሬ ግን እግዚአብሔር እኛን በመተው እንደ ፈለጉ ያደርጉን ዘንድ ለምድያማውያን አሳልፎ ሰጥቶናል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos