Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 27:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ክፉ ሰው ብርን እንደ ዐፈር ሊያጋብስ፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ሊከምር ይችላል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢሰ​በ​ስብ፥ ወር​ቅ​ንም እንደ ጭቃ ቢያ​ዘ​ጋጅ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 27:16
15 Referencias Cruzadas  

በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላ ይቈጠር ነበር፤


ንጉሥ አርጤክስስ የአይሁድ ጠላት የነበረውን የሃማንን ሀብት በሙሉ በዚያኑ ዕለት ለአስቴር ሰጣት፤ አስቴርም፥ መርዶክዮስ ለእርስዋ የቅርብ ዘመድ መሆኑን ለንጉሡ ነገረችው፤ መርዶክዮስም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወደ ንጉሡ ፊት መቅረብ ተፈቀደለት፤


ባለጸጋ አይሆንም፥ ሀብቱም ለብዙ ጊዜ አይቈይም፤ በምድር ላይም አይስፋፋም።


ልጆቹ እየተለማመጡ አባታቸው ከድኾች በግፍ የቀማውን ገንዘብ ይከፍላሉ።


ወርቅን ወደ ትቢያ ጣለው፤ የኦፊርንም ወርቅ እንደ ጅረት ድንጋይ ወርውረው፤


ከዚህ የተረፉትም በበሽታ ያልቃሉ፤ መበለቶቻቸው እንኳ አያለቅሱላቸውም።


ዳሩ ግን ክፉ ሰው የሰበሰበውን ልብስ ጻድቅ ይለብሰዋል፤ ያካበተውንም ብር ንጹሖች ይካፈሉታል።


ቤቶቻቸውን በወርቅና በብር ከሞሉ መሳፍንት ጋር አብሬ በተኛሁ ነበር፤


ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚተላለፍ ሀብት ያገኛል፤ የኃጢአተኞችን ሀብት ግን ቅን ሰዎች ይወርሱታል።


እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


ሰው ሁሉ እንደነዚህ ባሉት ሰዎች ላይ በመሳለቂያ እንቆቅልሽ እንዲህ ይላል፦ “ያንተ ያልሆነውን የምታግበሰብስ ወዮልህ! በመያዣነት በተወሰዱ ዕቃ ራስህን የምታበለጽገው እስከ መቼ ነው?”


እናንተ ከከተማው በታችኛው ክፍል የምትኖሩ ሁሉ ነጋዴዎቻችሁ ስለሚወገዱና በብር የሚነግዱ ሁሉ ስለሚጠፉ ይህን ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ‘ዋይ! ዋይ!’ እያላችሁ አልቅሱ።


ጢሮስ ለራስዋ መጠበቂያ ብዙ ምሽጎችን ሠርታለች፤ ብዛቱ እንደ ትቢያና እንደ ዐፈር የበዛ ብርና ወርቅ አከማችታለች።


ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት፥ በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ።


ሀብታችሁ ሁሉ በስብሶአል። ልብሳችሁንም ብል በልቶታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos