Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 30:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እንደ ሽቶ ቀላቅለህ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ሥራ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እነዚህን በቀማሚ እንደ ተሠራ እንደሚሸት ቅመም የተቀደሰ ቅብዐ ዘይት አድርግ፤ የተቀደሰ ቅብዐ ዘይት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በቀማሚ እንደሚቀመም ቅመም የተቀደሰ የቅባት ዘይት ታደርገዋለህ፤ የተቀደሰ የቅባት ዘይትም ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በቀ​ማ​ሚም ብል​ሃት እንደ ተሠራ ቅመም፥ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በቀማሚም ብልሃት እንደ ተሠራ ቅመም፥ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ታደርገዋለህ፤ የተቀደሰ የቅብዓት ዘይት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:25
18 Referencias Cruzadas  

ካህኑ ሳዶቅም ከተቀደሰው ድንኳን ይዞት የመጣውን የቅባት ዘይት መያዣ ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ በዚህን ጊዜ እምቢልታ ነፉ፤ ሕዝቡም ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!” አሉ፤


ከካህናቱም ወገኖች አንዳንዶቹ ቅመማቅመሙን የማዋሐዱን ኀላፊነት ወሰዱ።


በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ፥ እስከ ልብሱም ዘርፍ ድረስ እንደሚዘልቅ፥ መልካም መዓዛ እንዳለው የወይራ ዘይት ነው።


አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤ የተቀደሰ ዘይት ቀብቼም አነገሥኩት።


እንግዲህ እነዚህን ልብሶች ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው፤ በክህነት ያገለግሉኝም ዘንድ የወይራ ዘይት በመቀባት የክህነትን ማዕርግ ትሰጣቸዋለህ፤ ትቀድሳቸዋለህም፤


በመሠዊያው ላይ ካለው ደም ጥቂት፥ ከቅባቱም ዘይት ጥቂት ወስደህ በአሮንና በልብሱ ላይ በአሮን ልጆችና በልብሶቻቸው ላይ ርጨው፤ በዚህ ዐይነት እርሱና ልጆቹ ከነልብሶቻቸው ለእኔ የተለዩ ይሆናሉ።


የቅባት ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቀባው፤


ስድስት ኪሎ ግራም ብርጒድ ውሰድ ይህም ሁሉ በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ ይሁን፤ በዚህም ላይ አራት ሊትር ዘይት ጨምርበትና፥


በማንኛውም ተራ ሰው ላይ አይፍሰስ፤ ይህንንም የመሰለ ቅባት ለመሥራት በዚህ ዘዴ ከመጠቀም ተጠንቀቁ፤ ቅዱስ ስለ ሆነ እናንተም ቅድስናውን ዕወቁ።


እንደ ሽቶ የተቀላቀለ ዕጣን አድርገህ ተጠቀምባቸው። ንጹሕና ቅዱስ ይሆንም ዘንድ ጨው ጨምርበት።


የዕጣን መሠዊያውንና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን፥ የድንኳኑን በር መጋረጃ፥


የተቀደሰውን የቅባት ዘይትና መልካም መዓዛ ያለውንም ጥሩ ዕጣን እንደ ሽቶ ቀላቅሎ ሠራ።


“ከዚያም በኋላ ድንኳኑን ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር የቅባቱን ዘይት በመቀባት ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው፤ የተቀደሰም ይሆናል።


የሞቱ ዝንቦች ተቀምሞ የተሠራውን የዘይት ሽቶ ሊያገሙት ይችላሉ፤ እንዲሁም ትንሽ ሞኝነት ታላቅ ጥበብን ያጠፋል።


ከዚህም ቀጥሎ ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወስዶ የተቀደሰውን ድንኳንና በውስጡ ያሉትንም ነገሮች ቀባ፤ በዚህ ዐይነት ሁሉንም ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን አደረገው፤


“አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም የክህነት ልብሱን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበውን ኰርማ ሁለቱን የበግ አውራዎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ ያለበትን መሶብ፥ አብረህ አምጣ፤


ማኅበሩ በግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ከተበቃይ እጅ በመታደግ አምልጦ ወደነበረበት ወደ መማጠኛ ከተማዋ መመለስ አለበት፤ በዘመኑ ሊቀ ካህናት የሆነው ሰው እስከሚሞትበት ድረስ እዚያው መቈየት ይኖርበታል።


ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃንም ጠላህ፤ በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከጓደኞችህም ይበልጥ ደስታን በሚሰጥ ቅባት ቀባህ” ይላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos