Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “ለውጪው ክዳን ይሆኑ ዘንድ፥ አንደኛው ቀይ ቀለም ከተነከረ አውራ በግ ቆዳ፥ ሌላው ከተለፋ የፍየል ቆዳ ሁለት ተጨማሪ ክዳኖችን ሥራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ለድንኳኑ በቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ ልብስ አብጅ፤ በላዩም ላይ የአቆስጣ ቈዳ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአስቆጣ ቁርበት አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ለድ​ን​ኳ​ኑም መደ​ረ​ቢያ ከቀይ አውራ በግ ቍር​በት፥ ከዚ​ያም በላይ ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት አድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ለድንኳኑም መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት፥ ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአስቆጣ ቁርበት አድርግ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 26:14
14 Referencias Cruzadas  

በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።


ተለፍቶ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ የተለፋ የፍየል ቆዳ፥ የግራር እንጨት፥


በርዝመቱ በኩል ከእያንዳንዱ መጋረጃ ትርፍ ሆነው የቀሩት ግማሽ ሜትር ስፋት ያላቸው መጋረጃዎች በጐንና ጐን ተንጠልጥለው ድንኳኑን ይሸፍኑት።


ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ከፈይ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ እንዲሁም የለፋ ቊርበት ያለው ሁሉ ይዞ መጣ።


ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ የለፋ ቊርበት፥ የግራር እንጨት፥


ከውጪ በኩል መክደኛ ይሆኑ ዘንድ አንደኛውን ቀይ ቀለም ከተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፥ ሌላውንም ከለፋ ቊርበት ሌሎች ሁለት መጋረጃዎችን ሠሩ።


ከአውራ በግ ቆዳ ተሠርቶ ቀይ ቀለም የተነከረው መደረቢያ፥ ከለፋ ቆዳ የተሠራው መደረቢያ፥ ለመከለያ የተሠራው መጋረጃ፥


ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።


የእርሱ ክብር ከተማይቱን ከቀኑ የፀሐይ ቃጠሎ ይጋርዳታል፤ ከዝናብና ከዐውሎ ነፋስ መጠጊያና መሸሸጊያ ስፍራ ይሆናታል።


ጥበብ ቀሚስ አለበስኩሽ፤ ከምርጥ ቆዳ የተሠራ ጫማ አደረግሁልሽ፤ ሐር ሻሽ በራስሽ ላይ አሰርኩልሽ፤ ውድ የሆነ ካባ ደረብኩልሽ።


መቅረዙንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ በቈዳ መሸፈኛ ጠቅልለው በመሸከሚያ ተራዳ ላይ ያኑሩት።


የመገናኛውን ድንኳን የውስጥና የውጪ መሸፈኛ፥ ከላይ የሚደረበውን የተለፋ ስስ ቊርበት፥ የመግቢያውን በር መጋረጃ ይሸከማሉ፤


“ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos