Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በየማለዳው እያንዳንዱ የሚበቃውን ያኽል ይሰበስብ ነበር፤ ፀሐይ ከሞቀ በኋላ ግን በመሬት ላይ የቀረው ሁሉ ይቀልጥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በየማለዳው እያንዳንዱ የሚያስፈልገውን ያህል ሰበሰበ፤ ፀሓዩ እየበረታ በሄደም ጊዜ ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጥዋት ጥዋት እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ሰበሰበ፤ ፀሐይም በሞቀ ጊዜ ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሰውም ሁሉ ለየ​ራሱ ጥዋት ጥዋት ሰበ​ሰበ፤ ፀሐ​ይም በተ​ኰሰ ጊዜ ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሰውም ሁሉ ዕለት ዕለት የሚበላውን ያህል በጥዋት ለቀመ፤ ፀሐይም በተኮሰ ጊዜ ቀለጠ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 16:21
8 Referencias Cruzadas  

አንዳንዶቹ የሙሴን ቃል ባለመስማት ለዕለቱ ከሰበሰቡት ከፍለው አሳደሩ፤ በማግስቱም ጠዋት ተልቶ ተገኘ፤ በስብሶም ሸተተ፤ ሙሴም እጅግ ተቈጣቸው።


በስድስተኛው ቀን ለእያንዳንዱ ሦስት ኪሎ ይሰበስቡ ነበር፤ የማኅበሩ መሪዎች ሁሉ መጥተው ስለ ምግቡ ለሙሴ ነገሩት፤


በወጣትነትህ ዘመን ፈጣሪህን አስብ፤ ይህን ባታደርግ ግን ክፉ ቀን ይመጣብሃል፤ “ደስ አያሰኙኝም” የምትላቸው ዓመቶች ይደርሳሉ።


ባለህ ኀይል ሥራህን ሁሉ በትጋት ፈጽም፤ ወደ ሙታን ዓለም ከወረድህ በኋላ በዚያ ሥራና ሐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ የለም።


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos