Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አስቴር 5:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሡ፥ ንግሥት አስቴር በስተ ውጪ በኩል መቆምዋን በተመለከተ ጊዜ በፊቱ ሞገስን አግኝታ ስለ ነበር የወርቅ በትሩን ዘረጋላት፤ እርስዋም ቀረብ ብላ የወርቁን በትር ጫፍ ነካች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ንግሥት አስቴር በአደባባዩ ላይ ቆማ ሲያያት ደስ አለው፤ በእጁ የያዘውን የወርቅ ዘንግ ዘረጋላት፤ አስቴርም ቀረብ ብላ የዘንጉን ጫፍ ነካች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ንጉሡም ንግሥቲቱ አስቴር በወለሉ ላይ ቆማ ባየ ጊዜ በዓይኑ ሞገስ አገኘች፥ ንጉሡም በእጁ የነበረውን የወርቁን ዘንግ ለአስቴር ዘረጋላት፥ አስቴርም ቀርባ የዘንጉን ጫፍ ነካች።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 5:2
9 Referencias Cruzadas  

ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።


እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።


አስቴርም ሄጋይን ደስ አሰኘችው፤ በፊቱም ሞገስ አገኘች፤ ጊዜም ሳያባክን ወዲያውኑ ጥሩ ምግብ እንዲሰጣትና የሰውነትዋ ቅርጽ በመታሸት እንዲስተካከል በማድረግ በቊንጅና እንክብካቤ እንድትጠበቅ ወሰነ፤ ከምርጥ ሴቶችም መኖሪያ ቤት ከሁሉ የተሻለውን ክፍል መርጦ በመስጠት ከቤተ መንግሥት የተመረጡ ሰባት ደንገጡሮች ያገለግሉአት ዘንድ መደበላት።


“እንደሚታወቀው ሁሉ ወንድም ሆነ ሴት፥ ማንም ሰው ሳይጠራ ወደ ውስጠኛው የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ለመግባትና ንጉሡን ለማየት ቢሞክር በሞት ይቀጣል፤ እንግዲህ ሕጉ ይህ ሲሆን፥ ከንጉሡ አማካሪዎች እስከ ሕዝቡ ድረስ ማንም ሰው የሚያውቀው ጉዳይ ነው፤ በሕጉ መሠረት ከሞት ለመዳን የሚችለው ማንም ሰው ወደዚያ በሚገባበት ጊዜ ንጉሡ ፈቅዶ የወርቅ በትሩን ሲዘረጋለት ብቻ ነው፤ እኔ ግን ወደ ንጉሡ ለመግባት ከተጠራሁ እነሆ ሠላሳ ቀኖች አልፈውኛል።”


ንጉሡም የወርቁን በትር ዘረጋላት፤ እርስዋም ተነሥታ በፊቱ በመቆም እንዲህ አለች፤


ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ።


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱንም እንደ ወራጅ ውሃ ወደ ፈቀደው ይመራዋል። የንጉሥንም አእምሮ ይቈጣጠራል።


ትኲር ብሎ ወደ መልአኩ ተመለከተና በመደንገጥ “ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?” አለ። መልአኩም እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህና ለድኾች የምታደርገው ምጽዋት መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል፤


ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው። ንጉሡም በግብጽና በቤቱም ሁሉ ላይ አዛዥ አደረገው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos