Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አስቴር 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጾም በጀመረች በሦስተኛውም ቀን አስቴር ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳ በዙፋኑ ክፍል ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው የቤተ መንግሥት አደባባይ ገብታ ቆመች፤ ንጉሡም በዚያው ክፍል ውስጥ ከመግቢያው በር ፊት ለፊት በተዘረጋ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በሦስተኛው ቀን አስቴር የክብር ልብሷን ለብሳ በንጉሡ አዳራሽ ፊት ለፊት ባለው በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ አደባባይ ገብታ ቆመች። ንጉሡም አዳራሹ ውስጥ በመግቢያው ትይዩ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሦስተኛውም ቀን አስቴር ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳ በንጉሡ ቤት ትይዩ በንጉሡ ቤት በውስጠኛው ወለል ቆመች፥ ንጉሡም በቤቱ መግቢያ ትይዩ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በንጉሡ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




አስቴር 5:1
14 Referencias Cruzadas  

“ንግሥት አስጢን ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳና ዘውድ ጭና ወደዚህ እንድትመጣ አድርጉ” አላቸው፤ ንጉሡ ይህንን ያደረገበት ምክንያት ንግሥት አስጢን እጅግ የተዋበች ስለ ነበረች ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖችና ለእንግዶቹ ሁሉ እንድትታይ ፈልጎ ነበር።


እዚያም በሱሳ ከተማ የሚኖር መርዶክዮስ ተብሎ የሚጠራ አንድ አይሁዳዊ ነበር፤ እርሱ የያኢር ልጅ ሲሆን ከብንያም ነገድ የቂስና የሺምዒ ዘር ነበር።


“እንደሚታወቀው ሁሉ ወንድም ሆነ ሴት፥ ማንም ሰው ሳይጠራ ወደ ውስጠኛው የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ለመግባትና ንጉሡን ለማየት ቢሞክር በሞት ይቀጣል፤ እንግዲህ ሕጉ ይህ ሲሆን፥ ከንጉሡ አማካሪዎች እስከ ሕዝቡ ድረስ ማንም ሰው የሚያውቀው ጉዳይ ነው፤ በሕጉ መሠረት ከሞት ለመዳን የሚችለው ማንም ሰው ወደዚያ በሚገባበት ጊዜ ንጉሡ ፈቅዶ የወርቅ በትሩን ሲዘረጋለት ብቻ ነው፤ እኔ ግን ወደ ንጉሡ ለመግባት ከተጠራሁ እነሆ ሠላሳ ቀኖች አልፈውኛል።”


“ሄደህ በሱሳ የሚገኙትን አይሁድ በአንድነት ሰብስብ፤ ጾም ዐውጃችሁም ለእኔ ጸልዩ፤ እስከ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም ዐይነት ምግብ አትብሉ፤ ምንም ዐይነት መጠጥ አትጠጡ፤ እኔና ደንገጡሮቼም በዚሁ ዐይነት እንቈያለን፤ ከዚህም በኋላ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ደፍሬ ወደ ንጉሡ ዘንድ እገባለሁ፤ ይህን በማድረጌ ብሞትም ልሙት።”


መርዶክዮስም ተነሥቶ ሄደ፤ አስቴር በነገረችውም መሠረት ሁሉን ነገር አደረገ።


ንጉሡም “በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ከባለሥልጣኖቼ መካከል ማን አለ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ ሃማን ባዘጋጀው እንጨት ላይ መርዶክዮስን ይሰቅል ዘንድ የንጉሡን ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ ቤተ መንግሥቱ አደባባይ በመግባት ላይ ነበር፤


መርዶክዮስም ሰማያዊና ነጭ ልብሰ መንግሥት ለብሶ፥ ሐምራዊ ካባ ደርቦና ውብ የሆነ የወርቅ አክሊል ደፍቶ ከቤተ መንግሥት ብቅ አለ፤ በሱሳም ከተማ የሆታና የእልልታ ድምፅ አስተጋባ።


“እነሆ! እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች፥ እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ።


ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ።


ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሄደው እንዳይሰርቁትና ለሕዝቡም ‘እነሆ፥ ከሞት ተነሥቶአል’ እንዳይሉ መቃብሩ እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ አለበለዚያ የኋለኛው ማሳሳት ከመጀመሪያው ይልቅ የባሰ ይሆናል።”


በመንግሥቴም በማእድ ተቀምጣችሁ ትበላላችሁ፤ ትጠጣላችሁ፤ በዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።”


እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥኩ እንዲሁም ድል የነሣ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos