Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 2:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህም “ለሞኝ የሚደርሰው ዕድል ለእኔም ይደርሳል፤ ታዲያ፥ ይህን ያኽል ጥበበኛ የመሆኔ ትርፉ ምንድን ነው?” ብዬ በልቤ አሰብኩ። ወዲያውኑ “ይህ ሁሉ ከንቱ ነው!” አልኩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም በልቤ፣ “የሞኙ ዕድል ፈንታ በእኔም ላይ ይደርሳል፤ ታዲያ ጠቢብ በመሆኔ ትርፌ ምንድን ነው?” አልሁ። በልቤም፣ “ይህም ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እኔም በልቤ፦ በአላዋቂ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል፤ ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ? አልሁ። የዚያን ጊዜም በልቤ፦ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እኔም በልቤ፥ “አላ​ዋ​ቂን የሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲሁ እኔ​ንም ያገ​ኘ​ኛል፤ እኔም ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ?” አልሁ፤ የዚ​ያን ጊዜም በልቤ፥ “ይህ ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ፥ አላ​ዋቂ በከ​ንቱ መና​ገ​ርን ያበ​ዛ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እኔም በልቤ፦ ለሰነፍ የሚደርሰው ለእኔም ይደርሳል ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ? አልሁ። የዚያን ጊዜም በልቤ፦ ይህ ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 2:15
9 Referencias Cruzadas  

እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤


እነሆ በዚህ ዓለም ላይ የተደረገውን ነገር ሁሉ ተመለከትኩ፤ ይሁን እንጂ ሁሉ ነገር ከንቱ ሆኖ አገኘሁት፤ ሁሉም ነገር ነፋስን እንደ መጨበጥ ሆኖ ይቈጠራል።


እኔማ በልቤ “ከእኔ በፊት ኢየሩሳሌምን ከገዙት ሁሉ ይበልጥ ታላቅና የጥበብ ሰው ሆኛለሁ፤ የጥበብንና የዕውቀትን ምንነት መርምሬ አጥንቻለሁ” ብዬ ነበር፤


ጥበብ በበዛ መጠን ትካዜ ይበዛል፤ ዕውቀትም በበዛ መጠን ጭንቀትን ያስከትላል።


ጥበበኛው እንዲህ አለ፦ ሁሉ ነገር ከንቱ፥ እንዲያውም የከንቱ ከንቱ ነው፤ ሁሉም ነገር በፍጹም ከንቱ ነው።


ጥበበኛንም ሆነ ሞኝን ሁለቱንም ለረጅም ጊዜ የሚያስታውሳቸው አይገኝም፤ በሚመጣው ዘመን ሁላችንም የተረሳን ሆነን እንቀራለን፤ ጥበበኞችም ሆንን ሞኞች፥ ሁላችንንም ሞት ይጠብቀናል።


ብዙ በተናገርን መጠን ቁምነገሩ ያነሰ ነው፤ ስለዚህ የመናገር ጥቅሙ ምንድን ነው?


ታዲያ፥ ጥበበኛ ሰው ከሞኝ የሚሻልበት ምን ነገር አለ? ለድኻስ ሕይወትን ለመምራት መቻሉ የሚያተርፍለት ጥቅም ምንድን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos