Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ከሰሎሞን ጋር መገናኘት ይፈልጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የምድር ነገሥታት ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበብ ለመስማት ከሰሎሞን ጋራ መገናኘት ይፈልጉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የምድርም ነገሥታት ሁሉ ጌታ በልቡ ያኖረውን ጥበብ ለመስማት የሰሎሞንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የም​ድ​ርም ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በልቡ ያኖ​ረ​ውን ጥበ​ቡን ይሰሙ ዘንድ የሰ​ሎ​ሞ​ንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የምድርም ነገሥታት ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰሎሞንን ፊት ሊያዩ ይመኙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:23
19 Referencias Cruzadas  

እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።


በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ሰምተው የእርሱን ጥበብ ያዳምጡ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ይልኩ ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞን በዓለም ከሚገኝ ከማንኛውም ንጉሥ ይበልጥ ሀብታምና ጥበበኛ ነበር፤


ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፥ የልብስ፥ የጦር መሣሪያዎች፥ የሽቶ፥ የፈረሶችና የበቅሎዎች ስጦታዎችን ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር።


ጥበብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም የሚገኙት ከእርሱ ዘንድ ነው።


በዚያን ጊዜ የእሴይ (የዳዊት) ዘር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ ሕዝቦች እርሱን ይፈልጉታል፤ መኖሪያውም የተከበረ ይሆናል።


የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ ይኖራል፤ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኀይል መንፈስ፥ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።


እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።


የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በመንግሥትህ አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመነ መንግሥት እንደ አማልክት የሆነ ዕውቀት፥ ጥበብና ማስተዋል የሞላበት ሆኖ ተገኝቶአል፤ በዚህም ምክንያት አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆር የጠንቋዮች፥ የአስማተኞች፥ የጠቢባንና የኮከብ ቈጣሪዎች ሁሉ አለቃ አድርጎ ሾሞት ነበር።


ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።


እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።


መንፈስ ቅዱስ ለአንዱ ሰው በጥበብ የመናገር ችሎታን ይሰጠዋል፤ ለሌላው ሰው ደግሞ ያው መንፈስ በዕውቀት የመናገርን ችሎታ ይሰጠዋል፤


ክብር የሚገባው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን በይበልጥ ታውቁ ዘንድ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ።


ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።


ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos