Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እያንዳንዳቸው ሦስት ኪሎ በሚያኽል ንጹሕ ወርቅ የተለበጡ ሦስት መቶ አነስተኛ ጋሻዎችን አሠርቶ ነበር፤ እነዚህንም ሁሉ ጋሻዎች “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንዲሁም ከጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ትንንሽ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእነዚህም በእያንዳንዱ ጋሻ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበር። ንጉሡም ጋሻዎቹን “የሊባኖስ ደን” በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ አኖረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከጥፍጥም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም ጋሻ የገባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ፤ ንጉሡም የሊባኖስ ዱር በተባለው ቤት ውስጥ አስቀመጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከጥ​ፍ​ጥ​ፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በየ​አ​ን​ዳ​ን​ዱም ጋሻ የገ​ባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ፤ ንጉ​ሡም የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለው ቤት ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከጥፍጥም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም ጋሻ የገባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ፤ ንጉሡም የሊባኖስ ዱር በተባለው ቤት ውስጥ አኖራቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:16
5 Referencias Cruzadas  

በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፤


“የሊባኖስ ደን” ተብሎ የተጠራው አዳራሽ ርዝመቱ አርባ አራት ሜትር፥ ወርዱ ኻያ ሁለት ሜትር፥ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፤ አዳራሹም በእያንዳንዱ ረድፍ ዐሥራ አምስት ሆነው በሦስት ረድፍ የቆሙ አርባ አምስት ምሰሶዎች ነበሩት፤ በምሰሶዎቹም ላይ የተጋደሙ፥ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠሩ ሠረገሎችና በየመካከላቸው የገቡ ሳንቃዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም በላይ በምሰሶዎቹ የተደገፉ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ የእነዚህም ዕቃ ቤቶች ጣራ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፤


ስለዚህ ንጉሥ ሺሻቅ በድል አድራጊነት ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ፥ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ፥ ንጉሥ ሰሎሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፤


ንጉሥ ሰሎሞን እያንዳንዳቸው ሰባት ኪሎ በሚያኽል ንጹሕ ወርቅ የተለበጡ ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎችንና


እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ከዝሆን ጥርስ አንድ ትልቅ ዙፋን አሠርቶ በንጹሕ ወርቅ አስለበጠው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos