Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 23:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሌዋውያን ሰይፎቻቸውን በእጆቻቸው በመያዝ ዙሪያውን ሆነው ንጉሡን ይጠብቁት፤ ንጉሡ ወደሚሄድበትም ቦታ ሁሉ አብረው ይሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት የሚሞክር ማንኛውም ሰው ይገደል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሌዋውያኑም እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ በንጉሡ ዙሪያ ሁኑ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚገባ ማንም ሰው ይገደል፤ ንጉሡ በሚሄድበትም ቦታ ሁሉ ዐብራችሁት ሁኑ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሌዋውያንም የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን በዙሪያው ይክበቡት፤ ወደ ቤቱም የሚገባ ይገደል ንጉሡም ሲገባና ሲወጣ ከእርሱ ጋር ሁኑ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሌዋ​ው​ያ​ንም የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን በእ​ጃ​ቸው ይዘው ንጉ​ሡን በዙ​ሪ​ያው ይክ​በ​ቡት፤ ወደ ቤቱም የሚ​ገባ ይገ​ደል፤ ንጉ​ሡም ሲገ​ባና ሲወጣ ከእ​ርሱ ጋር ሁኑ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሌዋውያንም የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን በዙሪያው ይክበቡት፤ ወደ ቤቱም የሚገባ ይገደል ንጉሡም ሲገባና ሲወጣ ከእርሱ ጋር ሁኑ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 23:7
7 Referencias Cruzadas  

በአገልግሎት ላይ ከሚገኙት ካህናትና ሌዋውያን በቀር ማንም ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት የለበትም፤ ካህናትና ሌዋውያን ግን ለእግዚአብሔር የተለዩ ስለ ሆኑ መግባት ይፈቀድላቸዋል፤ የቀሩት ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመፈጸም ከቤተ መቅደሱ ውጪ ይሁኑ።


ሌዋውያንና የይሁዳ ሕዝብ ካህኑ ዮዳሄ የሰጣቸውን መመሪያ ሁሉ ፈጸሙ፤ ዮዳሄም አገልግሎታቸውን ፈጽመው በሰንበት ቀን ከሥራ ነጻ መሆን የሚገባቸው ሌዋውያን አላሰናበታቸውም ነበር፤ ስለዚህ ለዘብ ጥበቃ የሚሰማሩትና ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት እዚያው ስለ ነበሩ የጦር መኰንኖቹ በቂ ሰዎች ነበሩአቸው፤


ይሁን እንጂ ሰው በቊጣ ተነሣሥቶና ሆን ብሎ ሌላ ሰው ቢገድል፥ ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ።


የክህነቱንም ሥራ ያከናውኑ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፤ ከእነርሱ በቀር ሌላ ሰው ይህን ሥራ ለማከናወን ቢሞክር በሞት ይቀጣ።”


በመገናኛው ድንኳን በስተምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል የሚሰፍሩት ሙሴ አሮንና የአሮን ልጆች ነበሩ፤ በመቅደሱ ውስጥ ስለ እስራኤል ሕዝብ ለሚፈጸም ማንኛውም ዐይነት የአገልግሎት ሥነ ሥርዓት ኀላፊዎች እነርሱ ነበሩ፤ ማንም ሌላ ሰው ወደ መቅደሱ ቢቀርብ በሞት ይቀጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos