Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 23:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አሁን ማድረግ ያለብንም ይኸው ነው፤ ካህናትና ሌዋውያን በሰንበት ቀን አገልግሎታቸውን ለማከናወን በሚመጡበት ጊዜ ከእነርሱ አንድ ሦስተኛው እጅ የቤተ መቅደሱን ቅጽር በሮች ይጠብቅ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እንግዲህ እናንተ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ዕለት ተረኛ ከሆናችሁት ከእናንተ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ አንድ ሦስተኛው በሮቹን ጠብቁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋዊውያን ከሦስቱ አንዱ በመግቢያ በሮች ላይ ጠባቂዎች ሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነሆ፥ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ይህ ነው፤ በሰ​ን​በት ቀን ከም​ት​ገ​ቡት ከእ​ና​ንተ ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ከሦ​ስት አንድ እጅ በመ​ግ​ቢያ በሮች በረ​ኞች ሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋዊውያን ከሦስት አንድ እጅ በመግቢያ በሮች በረኞች ሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 23:4
8 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


ኀላፊነታቸውም የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በሚያከናውኑት ተግባር መርዳት፥ የአደባባዩንና የክፍሎቹን እንክብካቤ መጠበቅ፥ ንዋያተ ቅድሳትን ማንጻት፥ እንዲሁም አጠቃላይ የሆነውን የቤተ መቅደሱን አገልግሎት ማከናወን ነው።


እነዚህን ዘበኞች በመንደሮቻቸው የሚኖሩ ዘመዶቻቸው በየሰባቱ ቀን ተራ እየገቡ መርዳት ነበረባቸው፤


ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ የመጨረሻው አንድ ሦስተኛ እጅ የመሠረት ቅጽር በር ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ ይጠብቅ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ ይሰብሰቡ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos