Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አባታቸው ብዙ ወርቅና ብር እንዲሁም ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ሌላም ልዩ ልዩ ንብረት ሰጣቸው፤ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች እያንዳንዱን በአንዳንድ ከተማ ላይ ሾመ፤ ኢዮራም የበኲር ልጁ ስለ ሆነ አባቱ ኢዮሣፍጥ በእርሱ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አባታቸውም ብዙ የብርና የወርቅ፣ የውድ ዕቃዎችም ስጦታ እንዲሁም በይሁዳ ያሉትን የተመሸጉ ከተሞች ሰጣቸው፤ ነገር ግን መንግሥቱን ለኢዮራም ሰጠ፤ የበኵር ልጁ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አባታቸውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከበረም ዕቃ፥ በይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች ሰጣቸው፤ መንግሥቱን ግን የበኩር ልጁ ስለ ሆነ ለኢዮራም ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አባ​ታ​ቸ​ውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕቃ፥ በይ​ሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ግን የበ​ኵር ልጁ ስለ​ሆነ ለኢ​ዮ​ራም ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አባታቸውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከበረም ዕቃ፥ በይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች ሰጣቸው፤ መንግሥቱን ግን የበኵር ልጁ ስለ ሆነ ለኢዮራም ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 21:3
5 Referencias Cruzadas  

ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው።


ሮብዓም ጥበብ በተሞላበት ሁናቴ ለወንዶች ልጆቹ ኀላፊነትን በመስጠት፥ በተመሸጉት የይሁዳና የብንያም ከተሞች ሁሉ ላይ ሾማቸው፤ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ በለጋሥነት አደራጀላቸው፤ ከብዙ ሚስቶችም ጋር አጋባቸው።


ሮብዓም መኖሪያውን በኢየሩሳሌም አድርጎ ስማቸው ከዚህ በታች ለተመለከተው ለይሁዳና ለብንያም ከተሞች ምሽጎችን ሠራ፤


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን ከርስቱ ላይ ቀንሶ ከልጆቹ ለአንዱ ቢሰጥ ያ ርስት ለርሱና ለራሱ ቤተሰብ ጸንቶ ይቈያል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos