Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 18:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚህ ጊዜ ሁለቱ ነገሥታት ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰው በሰማርያ ቅጽር በር አጠገብ በውጪ በኩል በሚገኘው አውድማ በየዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያቱም ሁሉ በነገሥታቱ ፊት ሆነው የትንቢት ቃል ይናገሩ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ አልባሰ መንግሥታቸውን ለብሰው፣ በሰማርያ ቅጥር በር መግቢያ አጠገብ ባለው ዐውድማ ላይ በየዙፋናቸው ተቀምጠው፣ ነቢያቱ ሁሉ በፊታቸው ትንቢት ይናገሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ልብሰ መንግሥት ለብሰው በሰማርያ በር መግቢያ አጠገብ በአደባባይ በዙፋኖቻቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያትም ሁሉ በፊታቸው ትንቢትን ይናገሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ልብሰ መን​ግ​ሥት ለብ​ሰው በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ትም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ልብሰ መንግሥት ለብሰው በሰማርያ በር መግቢያ አጠገብ በአደባባይ በዙፋኖቻቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፤ ነቢያትም ሁሉ በፊታቸው ትንቢትን ይናገሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 18:9
12 Referencias Cruzadas  

ከእነርሱም አንዱ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ከብረት ቀንዶችን ሠርቶ አክዓብን “እግዚአብሔር ‘በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’ ይልሃል” አለው።


አክዓብም ኢዮሣፍጥን “ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ሌላ ልብስ እለብሳለሁ፤ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ” አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ።


ከዚህ በኋላ ንጉሥ አክዓብ ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለሥልጣኖች አንዱን ጠርቶ “ሚክያስን ፈልገህ በማግኘት በፍጥነት እንዲመጣ አድርግ” ሲል አዘዘው።


“የሙታን ዓለም የባቢሎንን ንጉሥ ለመቀበል ተዘጋጅታለች፤ የሙታን መናፍስትም ሁሉ እርሱን ለመቀበል ይንቀሳቀሳሉ፤ በምድር ላይ ኀያላን የነበሩ እጅ ይነሡታል፤ ነገሥታት የነበሩትም ከዙፋናቸው ይነሡለታል።


በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ።


“እኔም እየተመለከትኩ ሳለሁ ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ያ ጥንታዊው በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ፥ ጠጒሩም እንደ ነጭ ሱፍ ነበር፤ ዙፋኑና የዙፋኑ መንኰራኲር እንደሚነድ እሳት ይንበለበሉ ነበር።


ደግሞስ ምን ለማየት ወጣችሁ? የተዋበ ልብስ የለበሰውን ሰው ለማየት ነውን? የተዋበ ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰው ልጅ በክብር ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት በአዲሱ ዓለም የእኔ ተከታዮች የሆናችሁ፥ እናንተም፥ በዐሥራ ሁለት ዙፋኑ ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።


ነገር ግን ሰሎሞንስ እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ፥ ከእነርሱ እንደ አንዲቱ አለበሰም እላችኋለሁ።


ቦዔዝ በከተማው በር አጠገብ ወደሚገኘው መሰብሰቢያ አደባባይ ሄዶ ተቀመጠ፤ ከዚህ በፊት ቦዔዝ ስለ እርሱ የተናገረው የአቤሜሌክ የቅርብ ዘመድ ወደዚያው ቦታ መጣ፤ ቦዔዝም በስሙ ጠርቶ “ወንድሜ ሆይ! ወደዚህ መጥተህ አጠገቤ ተቀመጥ” አለው። እርሱም ወደዚያ ሄዶ ተቀመጠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos