Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 11:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም የተነሣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን በቅን መንፈስ ለማምለክ የፈለጉ ከመላው የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ብዙ ሰዎች ለቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ ከልባቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ሌዋውያኑን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለጌታ ለመሠዋት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ደግ​ሞም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ፈ​ለግ ልባ​ቸ​ውን የሰጡ ሁሉ እነ​ር​ሱን ተከ​ት​ለው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ደግሞም ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸውን የሰጡ ሁሉ እነርሱን ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 11:16
28 Referencias Cruzadas  

ለስሙ ተገቢ የሆነውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ወደ መቅደሱም መባ ይዛችሁ ቅረቡ፤ ግርማ በተመላ ቅድስናው ለእግዚአብሔር ስገዱ።


ዳዊትም “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና የእስራኤል ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርቡበት መሠዊያ ሊኖሩ የሚገባቸው በዚህ ስፍራ ነው” አለ።


እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ አገልግሉ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና እግዚአብሔርን ለማምለክ መገልገያ የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ አምጥታችሁ በውስጡ ማኖር ትችሉ ዘንድ ቤተ መቅደሱን ለክብሩ መሥራት ጀምሩ።”


ይህም ሁኔታ የይሁዳን መንግሥት አጠናከረ፤ ሦስት ዓመት ሙሉም የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን ረዱ፤ የንጉሥ ዳዊትንና የንጉሥ ሰሎሞንን መንገድ ተከትለው በሰላም ኖሩ።


የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ያመልኩትም ዘንድ በመስማማት ቃል ኪዳን ገቡ፤


የይሁዳ ሰዎች ሁሉ በፍጹም ልባቸው ይህን ቃል ኪዳን ስለ ገቡ ደስ ተሰኝተው ነበር፤ እግዚአብሔርንም አጥብቀው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር በመሆን በዙሪያቸው ሁሉ ሰላም እንዲኖር አደረገላቸው።


አምላኩ እግዚአብሔር ከንጉሥ አሳ ጋር መሆኑን ስላዩ፥ ከኤፍሬም፥ ከምናሴና ከስምዖን ነገዶች የሆኑ ብዙ ሰዎች ወደ አሳ መጥተው በግዛቱ ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ አሳም እነዚህን ሰዎች ሁሉ፥ እንዲሁም መላው የይሁዳና የብንያም ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤


ይህም ሁሉ ሆኖ አንዳንድ መልካም ነገር አድርገሃል፤ ይኸውም ሕዝቡ ያመልካት የነበረችውን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎችን ሁሉ ከምድሪቱ አስወግደሃል፤ የእግዚአብሔርንም ፈቃድ ለይተህ ለመፈጸም ጥረት አድርገሃል።”


ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤


ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ለመጸለይ ፈጥነው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ትሕትናን በማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም ፈቃደኞች ሆነው የመጡ ከአሴር፥ ከምናሴና ከዛብሎን ነገዶች አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፤


እግዚአብሔር መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ለመመለስ ቢያስብ፥


አምላኬ ሆይ! ልቤ ጽኑ ነው፤ ነቅቼ በሁለንተናዬ እዘምራለሁ፤ በዜማ አመሰግንሃለሁ።


በብዝበዛ አትመኩ፤ በቀማችሁትም ነገር ለመክበር ተስፋ አታድርጉ፤ ሀብታችሁ ቢበዛ እንኳ በእርሱ አትተማመኑ።


የቀሩት ግን እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ችላ በማለት አገልጋዮቻቸውንና እንስሶቻቸውን በሜዳ ተዉ።


ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ለማዳን ወሰነ፤ ፀሐይም እስክትጠልቅ ድረስ እርሱን ለማዳን የሚችልበትን ዘዴ ሁሉ ለማግኘት ሞከረ።


የሕዝቤ ኃጢአት ለእናንተ መበልጸጊያ በመሆኑ ሕዝቡ ኃጢአትን አብዝተው እንዲሠሩ ትፈልጋላችሁ።


ያላችሁበትን ሁኔታ አስቡ።


የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ከተማ ሄደው ‘ኑ! ከሠራዊት አምላክ ቸርነትን እንለምን፤ እኛም ወደዚያ መሄዳችን ነው!’ ይሉአቸዋል።


እርሱም ሄዶ እግዚአብሔር ጸጋውን ለሕዝቡ እንዴት እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉም በሙሉ ልብ ጸንተው ለጌታ ታማኞች ሆነው እንዲኖሩም መከራቸው።


ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።


እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ።


አሁን ግን ምድራችሁ የረከሰ ቢሆን የእግዚአብሔር ማደሪያ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ምድር ተሻገሩ፤ በመካከላችን ርስት ይኑራችሁ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ወይም በእኛ ላይ አታምፁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos