Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሮብዓምም በይሁዳ ግዛት በሚኖር ሕዝብ ላይ ብቻ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይሁን እንጂ ሮብዓምም በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት እስራኤላውያን ላይ ነገሠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በይሁዳ ከተሞች በተቀመጡት በእስራኤል ልጆች ላይ ግን ሮብዓም ነገሠባቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ግን ሮብ​ዓ​ምን በላ​ያ​ቸው አነ​ገሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በይሁዳ ከተሞች በተቀመጡት በእስራኤል ልጆች ላይ ግን ሮብዓም ነገሠባቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 10:17
8 Referencias Cruzadas  

ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ


ሮብዓምም በይሁዳ ግዛት በሚኖሩት ሕዝብ ላይ ብቻ ነገሠ።


እስራኤላውያን ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄአቸውን እንዳልተቀበላቸው በተገነዘቡ ጊዜ፥ “ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅስ ጋር ምን ግንኙነት አለን? እስራኤል ሆይ! ወደ እየቤትህ ሂድ! ዳዊት ሆይ የራስህን ቤት ጠብቅ!” ብለው መለሱለት። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደ የቤቱ ሄደ።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የጒልበት ሥራ የሚሠሩ ገባሮች ኀላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህን ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ።


ንጉሥ ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች የተውጣጡ አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ምርጥ ወታደሮችን ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የእስራኤልን ነገዶች ወግቶ ግዛቱን እንደገና በቊጥጥሩ ሥር ለማድረግ ዐቅዶ ስለ ነበር ነው።


እንዲሁም ጋሻና ጦር አከማቸ፤ በዚህም ዐይነት የይሁዳንና የብንያምን ግዛት በቊጥጥሩ ሥር አደረገ።


ለሮብዓም፥ እንዲሁም ለመላው የይሁዳና የብንያም ነገዶች


“የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ወስደህ ‘በእርሱ ላይ ለይሁዳና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ፤ ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ በእርሱ ላይ ‘ለዮሴፍ ማለት ለኤፍሬምና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos