Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 10:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ወጣቶቹም በሰጡት ምክር መሠረት “አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ!” ሲል መለሰላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱም ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን እጨምርበታለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” ብሎ እንደ ብላቴኖቹ ምክር ተናገራቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “አባቴ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ባ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን እጨ​ም​ር​በ​ታ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ እንደ ብላ​ቴ​ኖቹ ምክር ተና​ገ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 “አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፤ እኔ ግን እጨምርበታለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ፤” ብሎ እንደ ብላቴኖቹ ምክር ተናገራቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 10:14
15 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ውድቅ አድርጎ ሕዝቡን በማመናጨቅ መናገር ጀመረ፤


ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ይኸው ነው።


የእውነተኞች ሰዎች ሐሳብ የቀና ነው፤ የክፉዎች ምክር ግን አታላይነት ነው።


የጥል መነሻ መፍረስ እንደ ጀመረ ግድብ ነው፤ ስለዚህ ጥል ከማስከተሉ በፊት ክርክርን አቁም።


ሕፃን የሆነ ንጉሥና እየደገሱ ገና በማለዳ የሚሰክሩ መሳፍንት ያሉአት አገር ወዮላት


ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጠቢብ ይሁን ሞኝ ተለይቶ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ እኔ የደከምኩበትንና በጥበቤ ያተረፍኩትን ነገር ሁሉ ወስዶ ባለቤት ይሆናል፤ ይህም ከንቱ ነው።


ማናቸውም ነገር ከመጀመሪያው ይልቅ ፍጻሜው የተሻለ ነው፤ በትዕቢት ከሚናገር ሰው ይልቅ ትዕግሥተኛ ሰው ይሻላል።


እኛ በመንግሥትህ አስተዳደር ሥራ ላይ የተመደብን የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች፥ ዐቃብያነ ሕግ፥ እንደራሴዎች፥ አማካሪዎችና አገረ ገዢዎች የተስማማንበት አንድ ነገር አለ፤ ይኸውም ከአሁን ጀምሮ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ወደማንኛውም አምላክ ወይም ሰው ጸሎት እንዳይደረግ ዐዋጅ እንድታስነግር ነው፤ ይህንንም ዐዋጅ የሚተላለፍ ቢኖር በአንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል እዘዝ።


ነገር ግን መራራ ቅናትና ራስ ወዳድነት በልባችሁ ቢኖር አትመኩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።


እንደ ጊንጥ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ በጅራታቸው ውስጥ ሰዎችን ለአምስት ወር የሚጐዱበት ኀይል ነበራቸው።


ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤ የምድር ጊንጦችን ኀይል የመሰለ ኀይል ተሰጣቸው፤


እነርሱንም ቢሆን አምስት ወር ለማሠቃየት እንጂ ለመግደል ፈቃድ አልተሰጣቸውም፤ አንበጣዎቹ የደረሰባቸው ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ያለ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos