Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 21:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኤልዛቤልም መልእክቱን እንደ ተቀበለች ወዲያውኑ አክዓብን “ናቡቴ ሞቶአል፤ በል አሁን ተነሥተህ ሂድና ለአንተ ለመሸጥ እምቢ ያለውን የወይን ተክል ቦታ ርስት አድርገህ ውሰድ” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኤልዛቤልም በድንጋይ ተወግሮ መሞቱን ወዲያው እንደ ሰማች አክዓብን፣ “ናቡቴ በድንጋይ ተወግሮ ሞቷል፤ በል ተነሣና ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ ሊሸጥልህ ያልፈለገውን የወይን ተክል ቦታ በርስትነት ውሰደው” አለችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የአውራጆቹንም አለቆች ጉልማሶች ቆጠረ፥ ሁለት መቶም ሠላሳ ሁለት ነበሩ፥ ከእነርሱም በኋላ ሕዝቡን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ቆጠረ፥ ሰባትም ሺህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አክ​ዓ​ብም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ቹን አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ቈጠረ፤ ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለ​ትም ሆኑ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ የእ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ቈጠረ፤ ሰባት ሺህም ሆኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የአውራጆቹንም አለቆች ጕልማሶች ቈጠረ፥ ሁለት መቶም ሠላሳ ሁለት ነበሩ፤ ከእነርሱም በኋላ ሕዝቡን ሁሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ሁሉ፥ ቈጠረ፥ ሰባትም ሺህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 21:15
8 Referencias Cruzadas  

ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው።


“ናቡቴ ተወግሮ ተገድሎአል” የሚል መልእክትም ወደ ኤልዛቤል ላኩ።


አክዓብም የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ወዲያውኑ ተነሥቶ ሄደ።


ኤልዛቤልም “እንግዲህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ ሳለህ እንደዚህ መሆን ይገባሃልን? ይልቅስ ተነሥ፤ በመደሰትም እህል ውሃ ቅመስ፤ እኔ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እንድታገኝ አደርጋለሁ!” አለችው።


ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት።


አንተም የአክዓብ ልጅ የሆነውን ጌታህን ንጉሡን መግደል አለብህ፤ በዚህም ዐይነት የእኔን ነቢያትና ሌሎችንም አገልጋዮቼን የገደለችውን ኤልዛቤልን እበቀላታለሁ፤


ዐመፅና ግፍ ለእነርሱ እንደ መብልና እንደ መጠጥ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos