Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 6:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አሒጦብ ጻዶቅን ወለደ፤ ጻዶቅ አሒማዓጽን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አኪማአስ ሳዶቅን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አኪ​ጦ​ብም ሳዶ​ቅን ወለደ፤ ሳዶ​ቅም አኪ​ማ​ኦ​ስን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 6:8
19 Referencias Cruzadas  

ንግግሩንም በመቀጠል ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “ተመልከት፤ ልጅህን አሒማዓጽንና የአብያታርንም ልጅ ዮናታንን ይዘህ ወደ ከተማይቱ በሰላም ሂድ፤


ከዚህ በኋላ እርሱና አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤላውያን መሪዎች የሰጡትን ምክር ሑሻይ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ነገራቸው፤


የአብያታር ልጅ ዮናታንና የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ማንም እንዳያያቸው ስለ ፈሩ፥ ከኢየሩሳሌም አካባቢ ባለችው በዔንሮጌል ምንጭ አጠገብ ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይም ዘወትር ወደዚያ እየሄደች የሚሆነውን ነገር ሁሉ ትነግራቸው ነበር፤ ከዚያም በኋላ እነርሱ ሄደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።


የአቤሴሎም ባለሟሎች ወደዚያ ቤት መጥተው ሴቲቱን “አሒማዓጽና ዮናታን የት ናቸው?” ሲሉ ጠየቁአት። እርስዋም “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ስትል መለሰች። ሰዎቹም ፈልገው ሊያገኙአቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።


ከዚህ በኋላ የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ኢዮአብን “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው የሚገልጠውን መልካም ወሬ ይዤ ወደ ንጉሡ ልሩጥ” አለው።


አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው።


ሱሳ የቤተ መንግሥት ጸሐፊ ሲሆን፥ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤


የአሒጡብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቤሜሌክ ካህናት ነበሩ፤ ሠራያ ደግሞ ጸሐፊ ነበረ፤


በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡት፤ ከዚህ በኋላ እምቢልታ በመንፋት ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!’ በሉ።


ንጉሡም እርሱን ያጅቡት ዘንድ ካህኑን ሳዶቅን፥ ነቢዩን ናታንን፥ የዮዳሄን ልጅ በናያንና የቤተ መንግሥቱን ክብር ዘበኞች ልኮአል፤ እነርሱም ንጉሡ በሚቀመጥባት በቅሎ ላይ እንዲቀመጥ አድርገውታል።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፥ የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩ ናታን፥ ሺምዒ፥ ሬዒና የዳዊት የክብር ዘበኞች አዶንያስን አልደገፉም።


ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያን የሠራዊቱ አዛዥ፥ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾመ።


ንጉሥ ዳዊት የአሮንን ዘሮች እንደየሥራ ምድባቸው በቡድን በቡድን ከፈላቸው፤ ይህንንም ያደረገው የአልዓዛር ዘር በሆነው በሳዶቅና የኢታማር ዘር በሆነው በአቤሜሌክ ረዳትነት ነው።


መራዮት አማርያን ወለደ፤ አማርያ አሒጦብን ወለደ፥


አሒማዓጽ አዛርያስን ወለደ፤ ዓዛርያስም ዮሐናን ወለደ፤


የሳዶቅ ዘር የሆነው ሊቀ ካህናት ዐዛርያስም ንጉሡን፥ “ሕዝቡ ዐሥራቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመረ ወዲህ፥ እነሆ፥ በቂ ምግብ አለን፤ ብዙም ተርፎናል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ ባረከ እነሆ፥ ይህን ሁሉ በብዛት አግኝተናል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos