ሕዝቅኤል 29:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ በወንዞችህም ላይ ነኝ፥ የግብጽን ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴቬኔና እስከ ኢትዮጵያ ጠረፍ ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ስለዚህ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በወንዞችህ ላይ ተነሥቻለሁ፤ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል እስከ አስዋን ከዚያም እስከ ኢትዮጵያ ወሰን ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እኔ በአንተና በወንዝህ ላይ በቊጣ ተነሥቻለሁ፤ በሰሜን ከሚግዶል ከተማ አንሥቼ በደቡብ እስከ አስዋን ከተማ ድረስ፥ እንዲያውም እስከ ኢትዮጵያ ጠረፍ ድረስ ግብጽን በሙሉ ምድረ በዳ አድርጌ ባዶዋን አስቀራታለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ስለዚህ፥ እነሆ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ በጦርና በቸነፈር ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ። Ver Capítulo |