Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 22:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16-17 ወደ በለዓምም መጥተው፦ የሴፎር ልጅ ባላቅ፦ ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና፥ እባክህ፥ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ምንም አይከልክልህ፤ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ አለ ብለው ነገሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፤ “የሴፎር ልጅ ባላቅ ይህን እንድንነግርህ ልኮናል፤ ወደ እኔ ለመምጣት የሚያግድህ ምንም ነገር አይኑር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ በለዓምም መጥተው እንዲህ አሉት፦ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ይላል፦ ‘እባክህ፥ ወደ እኔ ለመምጣት ምንም ዓይነት ነገር አያግድህ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነርሱም ወደ በለዓም ሄደው የባላቅን መልእክት እንዲህ ሲሉ ነገሩት፤ “ወደ እኔ መምጣት እንዳትችል የሚያግድህ ነገር አይኑር!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ በለ​ዓ​ምም መጥ​ተው፥ “የሶ​ፎር ልጅ ባላቅ፦ እባ​ክህ ወደ እኔ መም​ጣ​ትን ቸል አት​በል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 22:16
5 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፥ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም፥ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው።


ንጉሡም ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደርገው፥ ብዙም ታላቅ ስጦታ ሰጠው፥ በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ ላይ ሾመው፥ በባቢሎንም ጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አለቃ አደረገው።


ባላቅም ደግሞ ከፊተኞች የበዙና የከበሩ ሌሎችን አለቆች ሰደደ።


ባላቅም በለዓምን፦ በውኑ አንተን ለመጥራት አልላክሁብህምን? ለምንስ ወደ እኔ አልመጣህም? በውኑ አንተን ለማክበር እኔ አልችልምን? አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos