Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 21:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እስራኤልም እነዚህን ከተሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስራኤልም በአሞራውያን ከተሞች ሁሉ በሐሴቦንና በመንደሮቹ ሁሉ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እስራኤልም ሐሴቦንና በአካባቢዋ ያሉትን ከተሞቹን ጨምሮ የአሞራውያንን ከተሞች በሙሉ በመያዝ እዚያው ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እስራኤልም እነዚህን ከተሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስራኤልም በአሞራውያን ከተሞች ሁሉ በሐሴቦንና በመንደሮቹ ሁሉ ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በዚህ ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ የአሞራውያንን ከተሞች ሐሴቦንንና በዙሪያ ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ጭምር ይዘው በዚያ ተቀመጡ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እስ​ራ​ኤ​ልም እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሁሉ ወሰደ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮቹ ሁሉ ተቀ​መጠ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 21:25
17 Referencias Cruzadas  

ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ እንደ ሚዳቋ ግለገሎች ናቸው።


ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮሁ ድምፃቸው እስከ ያሀፅ ድረስ ይሰማል፥ ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፥ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች።


ከእንግዲህ ወዲህ የሞዓብ ትምክሕት የለም፥ በሐሴቦን ላይ፦ ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት ብለው ክፉ ነገር አስበውባታል። መድሜን ሆይ፥ አንቺ ደግሞ ትጠፊአለሽ ሰይፍም ያሳድድሻል።


ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፥ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፥ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።


የሸሹ ደክመው ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፥ እሳት ከሐሴቦን ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአል የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአል።


ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሺቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።


እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበር፥ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።


ምርኮአቸውን፥ የሰዶምና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ የሰማርያንና የሴቶች ልጆችዋንም ምርኮ፥ በመካከላቸውም ያሉትን የምርኮኞችሽን ምርኮ እመልሳለሁ፥


የአሞራዊውንም ምድር ትወርሱ ዘንድ ከግብጽ ምድር አወጣኋችሁ፥ በምድረ በዳም አርባ ዓመት መራኋችሁ።


ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ከእጁ ወስዶ ነበር።


እስራኤልም እንደዚህ በአሞራውያን ምድር ተቀመጡ።


እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ሴባማ፥ ናባው፥ ባያን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን።


ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን አሳደዱአቸው፤ እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።


እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተዋጉ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ፥ ምድራቸውንም ወረሳችሁ፥ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።


እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አልወሰዳችኋቸውም ነበር?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos