Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 8:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የተደበቁትም ፈጥነው ከስፍራቸው ተነሡ፥ ኢያሱም እጁን በዘረጋ ጊዜ ሮጡ፥ ወደ ከተማይቱም ገብተው ያዙአት፥ ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይህን እንዳደረገም ያደፈጡት ሰዎች ከተደበቁበት ስፍራ በፍጥነት ወጥተው ወደ ፊት ሮጡ፤ ገብተው ከተማዪቱን ያዟት፤ ወዲያውኑም በእሳት አቃጠሏት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የተደበቁትም ፈጥነው ከስፍራቸው ተነሡ፥ ኢያሱም እጁን በዘረጋ ጊዜ ሮጡ፥ ወደ ከተማይቱም ገብተው ያዙአት፤ ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እጁንም በዘረጋ ጊዜ ሸምቀው የነበሩት ወታደሮች ከቦታቸው ተነሥተው ወደፊት ሄዱ፤ ወደ ከተማዋም በፍጥነት ገብተው በቊጥጥራቸው ሥር አደረጓትና ወዲያውኑ አቃጠሉአት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የተ​ደ​በ​ቁ​ትም ፈጥ​ነው ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነሡ፤ ኢያ​ሱም እጁን በዘ​ረጋ ጊዜ ወጡ፤ ወደ ከተ​ማ​ዋም ገብ​ተው ያዙ​አት፤ ፈጥ​ነ​ውም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 8:19
5 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ኢያሱን፦ ጋይን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁና በእጅህ ያለውን ጦር በላይዋ ዘርጋ አለው፥ ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ።


በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፥ ምርኮዋንና ከብትዋን ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፥ ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አስቀምጥ አለው።


የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፥ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም፥ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ተመለሱ።


የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከስፍራቸው ተነሥተው በበኣልታማር ተሰለፉ። ከእስራኤልም ተደብቀው የነበሩት ከስፍራቸው ከጊብዓ ሜዳ ወጡ።


ተደብቀውም የነበሩት ፈጥነው ወደ ጊብዓ ሮጡ፥ ተደብቀውም የነበሩት መጥተው ከተማውን ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos