Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በምሥራቅ ዮርዳኖስ፥ ከኢያሪኮም በስተ ምሥራቅ ከፍ ብሎ በሚገኘው በረሓማ አገር፥ በሮቤል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ቤጼርን፥ በጋድ ግዛት ውስጥ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ግዛት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን መርጠው ለዩ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 20:8
12 Referencias Cruzadas  

የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቶቹን አራት መቶ የሚያህሉትን ሰዎች ሰብስቦ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም “እግዚአብሔር በንጉሥ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ፤” አሉት።


ከአክዓብም ልጅ ከኢዮራም ጋር የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገልዓድ ሊጋጠም ሄደ፤ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቈሰሉት።


ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማርያዋ፥ ያሳና መሰማሪያዋ፥


ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰምርያዋ፥ መሃናይምና መሰማርያዋ፥


በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን።


ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።


በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።


በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።


ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰምርያዋን፥ በኤሽትራንና መሰምርያዋን፥ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።


ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰምርያዋን፥ ያሀጽንና መሰምርያዋን፥


ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos