Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 13:25 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ድንበራቸው ኢያዜር፣ የገለዓድን ከተሞች በሙሉ በረባት አጠገብ እስካለው እስከ አሮዔር የሚደርሰውን የአሞናውያን አገር እኩሌታ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ግዛታቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት ለፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የእነርሱም ግዛት ያዕዜርንና በገለዓድ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ የዐሞንን ምድር እኩሌታ ጨምሮ ከራባ በስተምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ይደርሳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 13:25
21 Referencias Cruzadas  

እንዲህም ሆነ፥ በዓመቱ መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹን እስራኤልንም ሁሉ ሰደደ። የአሞንም ልጆች አገር አጠፉ፥ ረባትንም ከበቡ፥ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።


ኢዮአብም የአሞንን ልጆች ከተማ ረባትን ወጋ፥ የውኃውንም ከተማ ያዘ።


ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ በጋድ ሸለቆ መካከል ባለችው በኢያዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአሮዔር ላይ ሰፈሩ።


ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ይሪያ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበር፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑአን ኀያላን ሰዎች ተገኙ፤


ሐሴቦንና መሰምርያዋ፥ ኢያዜርና መሰማርያዋ ተሰጡ።


የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች አዝነዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥተው ነበር፥ ቍጥቋጦቹም ተዘርግተው ባሕርን ተሻግረው ነበር።


ከተሞችዋ ለዘላለም የተፈቱ ይሆናሉ፥ ለመንጋ ማሰማርያ ይሆናሉ፥ መንጎች በዚያ ያርፋሉ የሚያስፈራቸውም የለም።


አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፥ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፥ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፥ አጥፊው በሰብልሽና በወይንሽ ላይ መጥቶአል።


ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች አገር ወደ ረባት ወደ ይሁዳም ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣ ዘንድ መንገድን አድርግ።


በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ በሰልፍም ቀን በጩኸት በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት አዳራሾችዋን ትበላለች፥


ሙሴም ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ሰደደ፤ መንደሮችዋንም ወሰዱ፥ በዚያም የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ።


ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥


ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና በአሞን ልጆች አቅራቢያ ስትደርስ አትጣላቸው አትውጋቸውም።


ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በረባት አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንንና የማዕካታውያንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥


ሙሴም ለጋድ ነገድ ለጋድም ልጆች በየወገኖቻቸው ርስት አድርጎ ሰጣቸው።


ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ፥


ሐሴቦንንና መሰምርያዋን፥ ኢያዜርንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡ።


ገለዓድ በዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፥ ዳንም ለምን በመርከብ ውስጥ ቀረ? አሴርም በባሕሩ ዳር ተቀመጠ፥ በወንዞቹም ዳርቻ ዐረፈ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos